የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ነዋሪዎችን እና የመስህብ መዳረሻዎችን ተደራሽ የሚያደርግ የ207 ኪሎ ሜትር መንገድ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

335
የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ነዋሪዎችን እና የመስህብ መዳረሻዎችን ተደራሽ የሚያደርግ የ207 ኪሎ ሜትር መንገድ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር በአማራ ክልል ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ፈጻሚነት በክልሉ መንግሥት ሙሉ ወጪ ኅብረተሰቡን እና የመስህብ ሀብቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመንገድ መሠረተ ልማቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
የተገነቡት የጠጠር መንገዶች ወልድያ መቸሬ አደባባይ እዜት አርሴማ ወገልጤና 102 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው 283 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበትና ከሲመኑ አቡነ ዮሴፍ እንጅፋት ወንዳች ሰቀላ 105 ኪሎሜትር የሚሸፍን 260 ሚሊዮን ብር ወጪ የሆነበት መንገድ ነው፡፡
ከሲመኑ አቡነ ዮሴፍ እንጅፋት ወንዳጅ ሰቀላ ያለው የመንገድ ሥራ ሁለት ወረዳዎችን፣ አራት ከተሞችንና 10 የገጠር ቀበሌዎችን እንዲገናኙ ያደርጋል፡፡
የተመረቁት መንገዶች ከወልዲያ ደላንታ ለመጓዝ ይፈጅ የነበረውን 222 ኪሎሜትር ወደ 102 ኪሎሜትር እንዲቀንስ አድርጓል፡፡
የመንገዶቹ ግንባታም የአካባቢውን አስቸጋሪ መልካ ምድርና የአርሶ አደሮችን እንግልት በውል ያገናዘቡ እንደሆኑ ተገልጿል።
በአካባቢው ያለውን የአጣና ምርት እና ሌሎች የንግድ እንቅስቃሴዎችን በማፋጠን የአርሶ አደሮችን ህይወት ለመቀየር፣ የቱሪዝም መዳረሻዎች የሆኑትን የሲርንዋ ቅድስት አርሴማ ገዳምንና የአቡነ ዮሴፍ አቡሃይ ጋራን ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡
በመንገዱ ምረቃ ላይም የአካባቢው ነዋሪዎች፣
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው፣ የፌዴራል ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ፀጋ አራጌ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዮሐንስ ቧያሌው፣ የወረዳና የዞን የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በመንገድ መሠረተ ልማት ችግር ምርታቸውን ወደ ገቢያ ለማቅረብ እንግልት ሲደርስባቸው የነበሩት የአካባቢው አርሶ አደሮችም መንገዱ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ያጋጥማቸው የነበረውን ችግር እንደሚፈታላቸው ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ሻምበል ወርቁ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleለክልሉ ብሎም ለሀገር ሠላም መረጋገጥ ሁሉም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ የሶማሌ ክልል የሠላምና አንድነት መድረክ ጥሪ አቀረበ፡፡
Next articleበኩር ጋዜጣ ግንቦት 02/2013 ዓ.ም ዕትም