
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሲሼኬዲ ጋር ተወያዩ።
ባሕር ዳር: ግንቦት 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የወቅቱን የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሲሼኬዲ እንዲሁም የልዑካን ቡድናቸውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በውይይቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎች” በመፈለግ እና በአሁኑ የሕብረቱ ሊቀመንበር አመቻችነት በአፍሪካ ሕብረት በሚመራው የሦስትዮሽ ድርድር ሂደት ቁርጠኛ መሆኗን በአጽንዖት ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት መካከል የትብብር እና የጋራ ልማት ተምሳሌት ሊሆን እንደሚችል እና በሁለቱም ሀገራት ላይ ምንም ጉዳት በማያስከትል መንገድ እንደሚከናወን ኢትዮጵያ ያላትን ጽኑ አቋም አስረድተዋል፡፡
በትብብር መርህ ማዕቀፍ (ዴክላሬሽን ኦፍ ፕሪንሲፕልስ) መሠረት ለሁሉም ወገኖች የሚጠቅም ስምምነት ላይ እንዲደረስ ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላት መገለጹን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ