በአጣዬና አካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደረገውን ድጋፍ በፍትሐዊነት ለማሰራጨት ድጋፉ በአንድ ማዕከል አንዲሆን እየተሠራ ነው፡፡

104
በአጣዬና አካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደረገውን ድጋፍ በፍትሐዊነት ለማሰራጨት ድጋፉ በአንድ ማዕከል አንዲሆን እየተሠራ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 03 /2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአጣዬና አካባቢው በተፈጸመው የተደራጀ ጥቃት ምክንያት የሰዎች ህይወት አልፏል፣ የአካል ጉዳት ደርሷል፣ ዘጎች ከመኖሪያ ቦታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ መንግሥት፣ መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች፣ በጎ ፈቃደኛ ማኅበራት እና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ለተጎዱና ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡
የሚደረገውን ድጋፍ በፍትሐዊነት ለማሰራጨት ድጋፉ በተማከለ መንገድ እንዲደረግ ታስቧል፡፡ ለዚህም የዞኑ መስተዳድር የገንዘብ፣ የምግብና ምግብ ነክ ያልኾኑ ድጋፎችን በማስተባበር ለሚያሰባስቡ አካላት ሕጋዊ ዕውቅና ሰጥቷል፡፡ ዕውቅና የተሰጣቸው አካላትም በከፍተኛ ተቆርቋሪነት በማስተባበር መንግሥት የሚያደርገውን ጊዜያዊ ድጋፍና በዘላቂነት ለማቋቋም እያከናወነ ያለውን ተግባር እያገዙ መሆኑን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ይሁን እንጂ ሕጋዊ ዕውቅና ሳይኖራቸው ሀብት የሚያሰባስቡ አካላት መኖራቸውን ነው የጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ ወርቃለማሁ ኮስትሬ የተናገሩት፡፡ እነዚህ አካላት በአንድ ማዕከል እንዲሰባሰቡና ድጋፉን እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ማኅበረሰቡም ድጋፍ ሲያደርግ ሕጋዊ እውቅና ለተሰጣቸው የሀብት አሰባሳቢዎች ብቻ መኾን እንዳለበትም አስገንዝበዋል። ከመንግሥት ዕውቅና ውጪ በሕገወጥ መልኩ የሚንቀሳቀስ ግለሰብም ሆነ ቡድን ሲገኝ ጥቆማ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል። በሕጋዊ መንገድ የእለት ደራሽ ድጋፍ በማሰባሰብ፣ በማስተባበርና በዘላቂነት ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በመንቀሳቀስ ላይ ላሉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ተፈናቃዮችን ለማሰባሰብ ከፍተኛ ሀብት እንደሚያስፈልግ በመግለጽም ድጋፋቸው በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ለሌላው መኖር ለምን ተሳነን”
Next articleበትግራይ የተረጋጋ ሕዝባዊ ሰላምና አስተዳደርን ለማረጋገጥ ሁሉም እገዛ እንዲያደርግ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ ጥሪ አቀረቡ፡፡