
ርዕሰ መስተዳድሩ ለቢሮ እና የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።
በዚህ መሰረት ፦
• አቶ ሙሉቀን አየሁ – የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኃላፊ
• ዶክተር መልካሙ አብቴ – የክለሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ
• ዶክተር ደስታ ተስፋው – የክልሉ የበይነ መንግስታት ኃላፊ
• አቶ ጎሹ እንዳላማው – የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ
• አቶ ቀለሙ ሙሉነህ እምሩ – የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ምክትል ቢሮ ኃላፊ
• አቶ ማሩ ቸኮል መንግስቱ – የክልሉ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር
• አቶ ፈንታው አዋየሁ – የክለሉ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ምክትል ሥራ አስኪያጅ
• አቶ ዘላለም ልየው – የክልሉ የጣና ሐይቅና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ምክትል ስራ አስኪያጅ
• ወይዘሮ ባንቺአምላክ ገብረማርያም – የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
• አቶ ሞላ ትእዛዙ – የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር
• አቶ ሀብታሙ መላክ – የርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ምክትል የጽህፈት ቤት ኃላፊ
• ወይዘሮ ውባለም እስከዚያው – የአማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታት መታሰቢያ ሃውልት ጽህፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ
• አቶ አዲስ በየነ – የአማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታት መታሰቢያ ሃውልት ጽህፈት ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ
• አቶ በለጠ ጌታነህ – የዕፅዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብአቶች ጥራት ቁጥጥር ኳራንታይን ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ታውቋል፡፡