የፌዴራል ፖሊስ ለ19ኛ ዙር በጦላይ ያሰለጠናቸውን ከ6 ሺህ በላይ የምልስ እና የምልምል ሰልጣኞችን አስመረቀ።

151
የፌዴራል ፖሊስ ለ19ኛ ዙር በጦላይ ያሰለጠናቸውን ከ6 ሺህ በላይ የምልስ እና የምልምል ሰልጣኞችን አስመረቀ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራል ፖሊስ ለ19ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የምልስ እና የምልምል ሰልጣኞችን መመዘኛውን አሟልተው የተገኙትን ዛሬ አስመርቋል።
በተመሳሳይ በ19ኛው ዙር ምልምል ሰልጣኞች ላይ የአፋር ክልል የልዩ ኃይል አባላትን አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ለሰልጣኞች የሥራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጠላቶች በጋራ ኾነው የሚሠሩበት ወቅት በመሆኑ ለሚኖረው ስምሪት ከነባሩ ሠራዊት ጋር በቅንጅት ለመሥራተት መዘጋጀት አለባችሁ ብለዋል።
ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ጥግ በነጻነት የመኖር እና ንብረት የማፍራት መብታቸው እንዲከበር ተመራቂዎች ከፍተኛ ኀላፊነት እንደሚጠበቅባቸው ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ተመራቂዎች ድርብ ኀላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ተመራቂ ሰልጣኞች የአድማ ብተና ትርዒት፣ የተኩስ ስልት፣ መሰናክል እና የጅምናዚየም ትርዒት አሳይተዋል ።
በከፍተኛ ሞራልና ተነሳሽነት ለሥራ ዝግጁ መሆናቸውንና በሀገሪቱ የዜጎች ደኀንነት እንዲጠበቅና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በቁርጠኝነት እንደሚሠሩም በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ያነጋገርናቸው ተመራቂዎች ተናግረዋል፡፡
በሥነ ምግባር እና በላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ምልምል ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
ተመራቂ የፌደራል እና የአፋር ክልል ፖሊስ አባላት ሕዝብ እና ሀገርን በታማኝነት እና በቅንነት ለማገልገል ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
ዘጋቢ:– ዳንኤል መላኩ– ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleኢዜማ ከባሕር ዳር ከተማ እና አካባቢው ከሚገኙ የሲቪል ማኅበራት ጋር ዉይይት አካሄደ፡፡
Next article“የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ምርጫዉን ለመታዘብ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀዋል” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ