የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን ለመተግብር የሚያስችል የ200 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈረመ።

325

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን ለመተግብር የሚያስችል የ200 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈረመ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ እና በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣
የሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና የኤርትራ ተጠሪ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ፈርመውታል።
ገንዘቡ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለመደገፍ ይውላል ፤ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስተባባሪነት
ለተቀረፁ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የተመደበ መሆኑም ተገልጿል።
ፕሮጀክቶቹን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የኮምዩኒኬሽን ባለስልጣን እና የሰላም
ሚኒስቴር የሚመሯቸው ናቸው።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የብድር ስምምነቱ ኢትዮጵያ አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የያዘችውን እቅድ እውን
ለማድረግ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
ለተግባራዊነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና የኤርትራ ተጠሪ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ
ውስጥ ማነቆ የሆኑ አሠራሮችን ለማዘመን ለሚደረገው ጥረት ብድሩ ለኢትዮጵያ እንደተሰጠ ጠቁመዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሀመድ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ “የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን” ቀርጻ
ወደ ትግበራ መገባቱን ጠቁመዋል።
በስትራቴጂው የኢንተርኔት ግንኙነት፣ ዲጂታል አገልግሎት እንዲሁም ፖሊሲና ስትራቴጂ ቅድሚያ የተሰጣቸው ጉዳዮች
መሆናቸውንም ተናግረዋል።
የብድር ስምምነቱ በ10 ዓመቱ የልማት እቅድ ውስጥ ለተካተተው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እውን መሆን የጎላ አስተዋፅኦ
እንዳለው ጠቁመዋል።
ገንዘቡ በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ውስጥ ቅድሚያ የተሰጣቸውን ዘርፎች ለመተግበር እንደሚያስችል
መግለጻቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቅባቸው በነበሩ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የምዝገባ ቀን ለተጨማሪ ሰባት ቀናት እንዲከናወን ምርጫ ቦርድ ወሰነ፡፡
Next articleኢትዮጵያዊያን በተለያዩ ዘውጎች ሊከፋፍሉ ከሚችሉ አስተሳሰቦች በመውጣት ለሰላምና ሉዓላዊነት በጋራ እንዲቆሙ ተጠየቀ።