
የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የፕርምየር ሊጉን ክብር በበላይነት ለማጠናቀቅ ማንም እርግጠኛ ሊሆን እንደማይገባ በማሳሰብ አርሰናል እና ቸልሲ አሁንም ከፉክክሩ ውጭ እንዳልወጡ አሰልጣኙ አሰገንዝበዋል፡፡

ቸልሲና አርሰናል የደረጃ ሰንጠረዡን በቀዳሚነት ከሚመራው ሊቨርፑል በ11 ነጥብ ዝቅ ብለው በአራተኛ እና አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ባለፉት አስር የውድድር ዓመታት (ጊዜያት) ውስጥ ስምንቱ ክለቦች በገና ሰሞን መሪ በመሆን የፕሪምየር ሊጉ አሸናፊ ሆነው ያጠናቀቁበት ነው፡፡ በሁለቱ ግን የተለየ ሁኔታ አጋጥሟል፡፡ በአውሮፓውያኑ 2008-2009 እና 2013-2014 የውድድር አመት በገና ሰሞን የበላይነቱን አስጠብቆ መጓዝ የቻለው ሊቨርፑል በስተመጨረሻ ሁለተኛ ሆኖ ነው ያጠናቀቀው፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ