“የመንግሥታቱ ድርጅት ሰሞኑን ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ወቅታዊና ተገቢ ነው” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

184

“የመንግሥታቱ ድርጅት ሰሞኑን ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ወቅታዊና ተገቢ ነው” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ሰሞኑን በኢትዮጵያ ጉዳይ ያወጣው መግለጫ የሀገሪቷን ወቅታዊ ሁኔታ የሚያሳይ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።

ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድሩ በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ስር ብቻ እንዲካሄድ የጸና አቋም እንዳላትም ተናግረዋል።

የሚኒስቴሩ ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸው ሰሞኑን የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ አንዳንድ አካላት በኢትዮጵያ ዙሪያ የነበራቸውን የተዛባ አመለካከት የቀየረ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለትግራይ ክልል የሚያደርገውን ሠብዓዊ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል።

ሰሞኑን ከመላው አውሮጳ የተወጣጡ ኢትዮጵያዊያን “ዲፌንድ ኢትዮጵያ” በሚል ቡድን ተደራጅተው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ቡድኑ በኢትዮጵያ ላይ የሚነዛውን የሐሰት ወሬ ለመከላከል እንዲሁም የኢትዮጵያን ትክክለኛ አቋም ለመግለጽ እየሰራ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ እና የሱዳ ድንበርን በተመለከተም አሁንም ኢትዮጵያ በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኗንም ገልጸዋል።

አምባሳደር ዲና ለመጪው ሀገራዊ ምርጫ የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ይልካል ተብሎ እንደሚጠበቅም አምባሳደሩ ተናግረዋል።

በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲም 593 ዜጎች ከጂዳ፣ 297 ከሪያድ እና 16 ደግሞ ከፑንትላንድ መመለሳቸውን ተናግረዋል።

የህዳሴ ግድቡ የሶስትዮሽ ድርድር በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ብቻ እንዲካሄድ ኢትዮጵያ የጸና አቋም እንዳላትም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በማብራሪያቸው አስታውቀዋል።

ግብጽና ሱዳን ድርድሩን ከአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ለማውጣት የሚያደርጉት ሙከራ ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም አክለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በሰሞኑ መግለጫው መንግስት በትግራይ ክልል ለሚያደርገው የሠብዓዊ ድጋፍ እውቅና በመስጠት ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል።

የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ፖለቲካዊ ነጻነት፣ የግዛት እና ሀገራዊ አንድነት በፅኑ እንደሚያከብር ማረጋገጡን መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየሕወሓት ቡድን ከስድስት ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ለወንጀል መፈጸሚያነት እንዳያውል መደረጉን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡
Next articleሕዝቡ በበዓል ግብይት ጊዜ በሐሰተኛ ገንዘብ እንዳይታለል ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ተገለጸ፡፡