የሕወሓት ቡድን ከስድስት ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ለወንጀል መፈጸሚያነት እንዳያውል መደረጉን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

247

የሕወሓት ቡድን ከስድስት ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ለወንጀል መፈጸሚያነት እንዳያውል መደረጉን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንደገለጸው የሕወሃት ሕገ-ወጥ ቡድን በሰሜን
ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ ባከናወነዉ የሀብት ክትትልና ምርመራ ሥራ ከ6 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ሕገ-
ወጥ ቡድኑ ለወንጀል መፈጸሚያነት ማዋል እንዳይችልና በሕገ-ወጥ መንገድ እንዳያሸሽ (እንዳይሰዉር) መከላከል ተችሏል፡፡
ከ97 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የሕወሃት ገንዘብ በሕግ አግባብ የዉርስ ዉሳኔ እንዲሰጥበት ለሚመለከተዉ አካል ተላልፏል
ብሏል፡፡
በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጀነራል አቶ ዓለምአንተ አግደዉ እንደገለጹት
የሕወሃት ሕገ-ወጥ ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈጸመበት ማግስት ጀምሮ ሕገ-ወጥ ቡድኑ ሲቆጣጠራቸዉ በነበሩና
ገንዘብና ንብረታቸዉን ለሕገ-ወጥ ዓላማዉ ሊጠቀምባቸዉ ይችላል በሚል በተጠረጠሩ ድርጅቶች እንዲሁም በጦርነት በተሳተፉ
የጦር መኮንኖችና ሌሎች ባለስልጣናት ላይ በተደረገ የሃብት ክትትልና ምርመራ ዉጤታማ ሥራዎች ተመዝግበዋል፡፡
ሀገራቸዉን ከድተዉ ከሕወሃት ጋር በመሰለፍ በጦርነት የተሳተፉ ዋና ዋና ተጠርጣሪዎች ገንዘብና ሃብት ላይ በተደረገ ክትትልና
ማጣራት ሥራ ከ54 ሚሊየን ብር በላይ እንዲሁም ሌሎች ብዛት ያላቸዉ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በፍርድ ቤት
ትዕዛዝ እንዲታገድ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡
በኤፈርት/ት.ም.ዕ.ት ሥር በሚተዳደሩ እና ተያያዥ የሆኑ የተለያዩ ድርጅቶች ላይ በተከናወነ የሀብት ክትትልና ምርመራ ሥራ
ከአራት ቢሊዬን ብር በላይ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማሳገድ እና ግምታቸዉ ከሁለት ቢሊዬን ብር በላይ የሆኑ 179 የደረቅና የፈሳሽ
ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ለማሸሽ ጥረት ሲያደርጉ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማዉጣትና የጋራ የሕግ ትብብር ጥያቄ ለጅቡቲ
መንግሥት በማቅረብ ወደ አገር ማስመለስ ተችሏል፡፡
ሕገ-ወጡ የሕወሃት ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ የኤፈርት /ት.ም.ዕ.ት ድርጅቶችን ገንዘብና ንብረት ለተጨማሪ
የወንጀል ተግባር መፈጸሚያ እንዳያዉል ከፍተኛ የመከላከል ሥራ መሥራት ተችሏል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ በሕወሃት ሕገ-ወጥ ቡድንና በቡድኑ ስር በነበሩ አመራሮች ቀጥተኛ ቁጥጥር ይደረግባቸዉ በነበሩና ቡድኑ
የድርጅቶችን ገንዘብ ለወንጀል መፈጸሚያ ሊያዉል ይችል የነበሩ ሦስት ሲቪል ማኅበራት ገንዘብ በቡድኑ ለሕገ-ወጥ ዓላማ
እንዳይዉል መከላከል እንደተቻለ አመላክተዋል፡፡
በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጄነራል በተከናወነዉ የሃብት ክትትልና ምርመራ ሥራ የሕወሃት የሆነ ብር ከ97
ሚሊየን ብር በላይ በማሳገድ ሕገ-ወጥ ቡድኑ ለወንጀል ተግባር እንዳይጠቀምበት እና ማሸሽ እንዳይችል መከላከል መቻሉም
ተገልጿል፡፡
ቡድኑ ኀይልን መሠረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ላይ መሳተፉን መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከምዝገባ የሰረዘዉ
በመሆኑ ይህንን ገንዘብ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 99 (2) እና (3) መሰረት ዕዳዉን ሸፍኖ የሚተርፍ የፓርቲዉ ገንዘብ
ካለ ለሥነ-ዜጋና መራጮች ትምህርት እንዲዉል በምርመራ ከተሰባሰቡ ማስረጃዎች ጋር አባሪ በማድረግ መጋቢት 17/2013
ዓ.ም ለቦርዱ እንዲተላለፍ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡
ቀሪ ሥራዎችን ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮና ሌሎች ከሚመለከታዉ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ትኩረት ተሰጥቶ
እየተሠራ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየዓባይ ውኃ ፍትሐዊ አጠቃቀም ዳግማዊ የፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄ።
Next article“የመንግሥታቱ ድርጅት ሰሞኑን ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ወቅታዊና ተገቢ ነው” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር