እንጅባራ ከተማ ሊገባ የነበረ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፋግታ ለኮማ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ::

506
እንጅባራ ከተማ ሊገባ የነበረ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፋግታ ለኮማ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ::
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 17/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ወደ እንጅባራ ከተማ ሚያዝያ 17/2013 ዓ.ም ሊገባ የነበረ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና ጥይት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፋግታ ለኮማ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ:: 900 የብሬን፣ 120 የክላሽ ጥይቶች፣ አንድ የቱርክ ሽጉጥ እና 43 የተለያዩ ስለታማ ቁሳቁስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጽሕፈት ቤት ኃላፊው ኮማንደር የትዋለ በለጠ ተናግረዋል፡፡
በእንጅባራ ከተማ ይካሄዳል ከተባለው ሰልፍ ጋር ተያይዞ የወረዳው ፖሊስ ዛሬ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ህገወጥ መሳሪያው በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድተዋል።
የሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር ኅብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመሰለፍ ሊሠራ እንደሚገባም ኮማንደር የትዋለ አሳስበዋል። በአሁኑ ወቅት ኅብረተሰቡ ከምንጊዜዉም በላይ ተደራጅቶ አካባቢዉን በንቃት መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋለው የጦር መሣሪያዎች ጋር የተያዙ ተጠሪጣሪዎችን ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑንም ኮማንደሩ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡- ቡሩክ ተሾመ
ፎቶ፡ ከፋግታ ለኮማ ወረዳ ኮምዩኒኬሽን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበቻግኒ ራንች ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ይነሳ የነበረው የሰብዓዊ ድጋፍ ፍትሐዊት ጥያቄ መፈታቱን ተፈናቃዮች ገለጹ፡፡
Next articleʺሆሳዕና በአርያም መድኃኒት በሰማይ”