
ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ማኅበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 16/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ እና አካባቢው በተፈጸመ ጥቃት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል፡፡ ይህንንም አስመልክቶ “ደራሽ ለአጣዬ” በሚል በአጣየ እና አካባቢው ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አሰባሳቢ በማቋቋም የተለያዩ ድጋፎችን የማሰባሰብ ሥራ እየተሠራ ይገኛል፡፡
የድጋፉ አሰባሳቢ አባል ገነቱ ደገፉ እንዳሉት ‹‹ኑ ሀገር እንሥራ፤ አንድ ሰው አንድ ቆርቆሮ፣ አንድ ሰው አንድ ቁምጣ ሲሚንቶ ›› በሚል መልዕክት አጣዬን መልሶ ለመገንባት ከሚያዝያ 14/2013 ዓ.ም ጀምሮ ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡
ዓላማውም አጣዬን በመገንባት ማኅበረሰቡን ወደ ነበረበት ለመመለስ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ዜጎች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን አቶ ገነቱ ተናግረዋል፡፡
በአካል ድጋፍ ማድረግ የማይችሉ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ዜጎች በአቢሲኒያ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 63477028 እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጭር የሂሳብ ቁጥር 6714 ወይም 1000397926714 ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
የድጋፍ ማሰባሰቢያ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች በቱሪዝም አስጎብኝ ገነቱ ደገፉ፣ በባለሀገሩ አስጎብኝ ድርጅት ባለቤት ተሾመ አየለ እና በጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ግሩም የተከፈተ መሆኑን አቶ ገነቱ ነግረውናል፡፡
በቀጣይ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ማንኛውም ማኅበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ተፈናቃዮችን አስጠልለው ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ፎቶ፡- ከባለሀገሩ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ