ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም በሚል የኢትዮጵያዊያን ግብረ ኃይል በአውሮፓ ተቋቋመ፡፡

157
ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም በሚል የኢትዮጵያዊያን ግብረ ኃይል በአውሮፓ ተቋቋመ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአውሮፓ አንዳንድ የፓርላማ አባላትና መንግሥታት እያስተጋቡ ያሉትን የተዛባ መረጃ ለመከላከል በዲፕሎማሲ፣ በማኀበራዊና በዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙኀን እየተሰራጨ ያለውን ሀሰተኛ መረጃ ለማረምና በሎጅስቲክስ ማሰባሰብ ላይ ያተኮረ ግብረ ኀይል ነው የተቋቋመው፡፡
በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ግብረ ኃይሉ ከሰባ በላይ ከፍተኛ ምሁራንን እና ወጣት የማኀበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን አሰባስቧል ብለዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም ግብረ ኀይል በአውሮፓ ደረጃ በመቀናጀት የፓርላማ አባላትን፣ ቲንክ ታንክ ቡድኖችን እና ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙኀን የሚያሳድሩትን ተጽእኖ በቀላሉ መቀነስ ይችላል ብለዋል፡፡
በትግራይ ክልል የተወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ ተከትሎ በአንዳንድ አካላት የተከፈተውን የተዛባ መረጃ የማሰራጨት ተደጋጋሚ ጥረትን ለማረምና የፓርላማ አባላትን እና መገናኛ ብዙሃን የያዙትን የተሳሳተ አቋም ለማስተካከል መደራጀቱ ከፍተኛ አቅምን ይፈጥራል ነው ያሉት።
አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት የፓርላማ አባላት እና መገናኛ ብዙኀን በውጪ ካለው የህወሃት ርዝራዥ ጋር በቀጥታ በመናበብ የሚያቀርቡት መረጃ ትክክለኛ አለመሆኑን ለማስረዳት በውጪ ያለው ኢትዮጵያዊ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊውያን ተቀናጅተው መስራት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
አምባሳደር ተፈሪ ግብጽና ሱዳን ከግድቡ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ እያራመደች ያለውን መርህ የተከተለ አሠራር እጅ በመጠምዘዝ ለማደናቀፍ የሚያደርጉት ሴራ ተጠናክሮ በመቀጠሉ ኢትዮጵያዊያን ይበልጥ ተቀናጅተው በመመከት ለሀገራቸው ብሔራዊ ጥቅም መቆም እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የዲጂታል ዲፕሎማሲና ሌሎች ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ ኢትዮጵያውያኑ ገልጸዋል፡፡ የመረጃ ምንጭ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከለንደን ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአማራ ላይ የተሠራውን የሀሰት ትርክት ለመቀየር መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባው የፖለቲካ ምሁር ተናገሩ፡፡
Next article“እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ የሕዝቡን ደኅንነት ለማረጋገጥ በቅንጅት መሥራት መቻል አለበት እንጂ መወነጃጀል መፍትሔ አያመጣም” መኮንን አለኸኝ (ዶክተር)