
በባሕር ዳር፣ በደብረ ማርቆስ እና ወልደያ ከተሞች በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ማንነትን መሰረት ያደረገ ግድያ የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 12/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በከተሞቹ እየተካሄዱ በሚገኙ ሰላማዊ ሰልፎች በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ማንነትን መሰረት ያደረጉ ግድያዎችንና መፈናቀሎችን በመቃወም፣ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቱን አውግዘዋል፡፡
በየከተሞቹ የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን እንዳደረሱን በሰላማዊ ሰልፎቹ በተለያዩ አካባቢዎች በአማራዎች ላይ የሚፈጸም ግድያ ይቁም፣ አማራን ማሳደድ ይቁም፣ በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያና መፈናቀል መንግሥትን ሊያሳስበው ይገባል፣ህጻናትን መግደልና ከተማ ማፍረስ ጀግንነት አይደለም የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችም ተላልፈዋል፡፡





ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ