
ኢትዮጵያና ሩስያ በሰላማዊ የኑክሌር ኃይል አጠቃቀም ያላቸው ትብብር እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 07/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያና ሩስያ በሰላማዊ የኑክሌር ኃይል አጠቃቀም ዙሪያ የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን በሞስኮ ተፈራርመዋል፡፡
የኑክሌር ኃይል በተመለከተ አዎንታዊ የሕዝብ አስተያየትን ለማስያዝ እና በኢትዮጵያ የኑክሌር ኃይል መስክ በትምህርት እና በስልጠና ትብብር መሥራት ላይ ያተኮረ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈርመዋል፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ እና የሩስያ የኑክሌር ኃይል ትብብር ኮርፖሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ኒኮላይ ስፓስኪ ናቸው፡፡
ምንጭ፡- በሩስያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ