ትናንት ምሽት በአጣዬ ከተማ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር እየተረጋጋ ነው፡፡ ካራቆሬን ለማረጋጋት የፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት እየሠሩ መሆኑንም አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

847
ትናንት ምሽት በአጣዬ ከተማ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር እየተረጋጋ ነው፡፡ ካራቆሬን ለማረጋጋት የፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት እየሠሩ መሆኑንም አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 07/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ትናንት ምሽት ከ 2 ሰዓት ገደማ ጀምሮ በአጣዬ ከተማ እና ካራቆሬ የጸጥታ ችግር መፈጠሩን የኤፍራታና ግድም ወረዳ አስተዳደር አስታውቋል፡፡ ችግሩ ቀደም ብሎ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም ጀምሮ በተደራጀና በታቀደ መልኩ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር የተያያዘ መሆኑን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ደምሰው መሸሻ ተናግረዋል፡፡
ከአጣዬና ካራቆሬ በተጨማሪ አላላ እና ጀብሃ አካባቢዎች አዝማሚያ መኖሩን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው በሁሉም የወረዳው አካባዎች አሁንም የጸጥታ ስጋቱ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡ የትናንት ምሽቱ የጸጥታ ችግር በአጣዬ ከተማ ቤት መቃጠልን ምክንያት በማድረግ የተነሳ ሲሆን በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስም ምክንያት ኾኗል፡፡
በአካባቢው የሚገኝ የመንግሥት የጸጥታ ኀይል ጉዳዩን በትዕግሥት ሲከታተል እንደነበር ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው ዛሬ ጠዋት መከላከያ ርምጃ ወስዶ በተለይ አጣዬ ከተማን ማረጋጋት እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡ በአጣዬ ከተማ ተኩስ ባይኖርም በከተማው አቅራቢያ በሚገኙ የገጠር አካባቢዎች የተኩስ ድምጽ እየተሰማ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ በካራ ቆሬም እስከ ቅርብ ሰዓት ድረስ ችግሩ መቀጠሉን ጠቅሰዋል፡፡
የመንግሥት የጸጥታ አካላት በተለይ የመከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ችግሩን ለመቆጣጠር እየሠሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ከዚህ በፊት በስልጠና ጭምር የሚታገዙ ኀይሎች ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጽሙ መንግሥት አስተማሪ ርምጃ አለመወሰዱ አሁንም ተደጋጋሚ ችግሮች እንዲፈጠሩ ዕድል የሰጠ መሆኑን አቶ ደምሰው አንስተዋል፡፡ ችግሩን ሊያስቆም የሚችል ርምጃ መውሰድ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአሠራር እና በስርጭት መዛባት የመጣውን የኑሮ ውድነት ለመሻገር በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ የምጣኔ ሀብት ምሁር ተናገሩ፡፡
Next articleኢትዮጵያና ሩስያ በሰላማዊ የኑክሌር ኃይል አጠቃቀም ያላቸው ትብብር እንደሚቀጥል ተገለጸ፡፡