የኢትዮጵያ ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲን ለመከለስ ግብዓት እየተሰባሰበ ነው፡፡

278
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲን ለመከለስ ግብዓት እየተሰባሰበ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 06/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ለመከለስ የክልል የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ቢሮ ኀላፊዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የወጣቶች ፌዴሬሽን እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ህይወት ኃይሉ ባስተላለፉት መልእክት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ የወቅቱ የሀገሪቱን እና የዓለምን ነባራዊ ሁኔታና የወጣቶችን ፍላጎትና ጥያቄ ባገናዘበ መልኩ ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
በ1995ዓ.ም የተቀረጸው ብሔራዊ የወጣቶች ፖሊሲ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ሳይደረግበት የቆየ እንደመሆኑ መጠን የወጣቶችን መብት ማስከበር፣ በየደረጃው በሚካሄዱ የልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ከማስቻል አኳያ ሰፊ ክፍተትና ውስንነት የሚስተዋልበት ነው ብለዋል፡፡ ፖሊሲው በአፈጻጸም ላይ ከፍተኛ እንቅፋትና ጫና እየፈጠረ በመሆኑ የወጣቶችን ፖሊሲ መከለስ አስፈላጊ ሆኗል ነው ያሉት፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ወጣቶች ፖሊሲን ለመከለስ በተዘጋጀ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ወጣቶችና የወጣቶች ስብዕና ግንባታ፣ የወጣቶች ሥራ አጥነት ጉዳይ፣ ወጣቶችና ጤና፣ ወጣቶችና ትምህርት እና ሌሎች ጉዳዮች ለውይይት ቀርበዋል፡፡ ያሉ ምቹ ሁኔታዎች፣ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይም ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ወጣቶች ፖሊሲ ጠቀሜታ፣ ወቅታዊነት እና አካታችነትን አስመልክቶ ምክክር መደረጉን ከሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleባለፉት 9 ወራት ከወጭ ንግድ 2 ነጥብ 45 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
Next articleበአሠራር እና በስርጭት መዛባት የመጣውን የኑሮ ውድነት ለመሻገር በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ የምጣኔ ሀብት ምሁር ተናገሩ፡፡