
ባሕር ዳር፡ መስከረም 6/2012 ዓ.ም (አብመድ) የዘንድሮው የጣና ሽልማት ወደ 21 ዘርፍ ክፍ ማለቱ ተገለጸ፡፡ የሽልማቱ ዓላማ ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር ለሚጠቀሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እውቅና መስጠት ነው፡፡ ባለፈው ዓመት በ16 ዘርፎች ነበር ሽልማት የሰጠው፡፡
ዘንድሮ ዘርፉን አስፍቶ በ21 መስኮች ሽልማት እንደሚሰጥ የዘመራ ማስታወቂያ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ እና የሽልማት ሥነ ስርዓቱ አስተባባሪ አቶ ደምስ አያሌው ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ ሽልማቱ ጥቅምት 1/2012 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ እንደሚካሄድ ተገልጧል፡፡
ለተሸላሚዎች ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነፃ የትምህርት እድል እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡
በዚህ ዓመት ለሚከናወነው የሽልማት ሥነ ስርዓት በየዘርፉ ለመጨረሻ ዙር የተመረጡት እጩዎች 68 መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት በቀጣይ ዓመት መርሀ ግብሩን ወደ ትልቅ ደረጃ ለማሸጋገር መታሰቡን አቶ ደምስ ተናግረዋል፡፡
የጣና ሽልማት በ2009 ዓ.ም ነው መሰጠት የተጀመረው፡፡
ዘጋቢ፡- ኪሩቤል ተሾመ