ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአጼ ቴዎድሮስን የታሪክ አሻራ ስፍራዎች የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮጀክት አዘጋጀ።

276
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአጼ ቴዎድሮስን የታሪክ አሻራ ስፍራዎች የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮጀክት አዘጋጀ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአጼ ቴዎድሮስን የታሪክ አሻራ ስፍራዎች በመጠበቅና በመንከባከብ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የሚያስችል የአምስት ዓመት የልማት ፕሮጀክት ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
እስከ 280 ሚሊዮን ብር የሚጠይቀው ፕሮጀክት 8 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል ለመፍጠር እንደሚያስችል በፕሮጀክቱ ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ላይ ተገልጿል።
በዩኒቨርሲቲው የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ረዳት ፕሮፌሰር ግርማ ታያቸው እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ “የቋራ መቅደላ ማህበረሰብ አቀፍ ኢኮ ቱሪዝም” በሚል ስያሜ የሚተገበር ነው።
በፕሮጀክቱ ከአጼ ቴዎድሮስ የትውልድ ስፍራ ቋራ ጀምሮ ለሀገር አንድነት ሲሉ መስዋዕት የሆኑበትን የመቅደላ አምባ የሚደርሱ ታሪካዊ ስፍራዎችን ለቱሪዝም ልማት ለማዋል የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።
ቋራን፣ ደረስጌ ማርያምን፣ ጋፋትንና መቅደላን ያካተተው ፕሮጀክቱ የአጼ ቴዎድሮስን ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ አሻራ የሆኑትን ቅርሶች በመጠበቅና በመንከባከብ አለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን ዓላማ ያደረገ ነው።
የአጼ ቴዎድሮስ ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ እሴቶች የሆኑ ታሪካዊ ስፍራዎች በቂ ጥበቃና ትኩረት የተሰጣቸው ባለመሆኑ ቅርሶቹ ለአደጋ መጋለጣቸውንም ፕሮፌሰር ግርማ ጠቁመዋል፡፡ ዘገባው የኢዜአ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
May be an image of 1 person and sitting
0
People Reached
42
Engagements
Boost Post
38
2 Comments
2 Shares
Like

Comment
Share
Previous articleየሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዕውን እንዳይሆን የሚሹ ኀይሎች አካባቢውን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ እየሠሩ ነው፡፡
Next articleየኮሮናቫይረስ ምርመራ ያቋረጡ ዩኒቨርሲቲዎች የችግሩን አሳሳቢነት ተገንዝበው ምርመራ እንዲጀምሩ የአማራ ኀብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጠየቀ፡፡