ትናንት ምሽት በተካሄደው የካራባዎ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በኢትሀድ ብሪቶን አልቢዮንን የጋበዘው ማንቸስተር ሲቲ በከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ 9ለ0 አሸንፏል፡፡

462

ትናንት ምሽት በተካሄደው የካራባዎ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በኢትሀድ ብሪቶን አልቢዮንን የጋበዘው ማንቸስተር ሲቲ በከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ 9ለ0 አሸንፏል፡፡

የሲቲን ቀዳሚ ግብ ዲብሮይን በ5ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፤ ሌላኛው የሲቲ ተጫዋች ጋብሬል ጀሰስ ደግሞ በ30ኛ፣ 34ኛ፣ 57ኛ እና 65ኛ ደቂቃዎች አራት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡ ቀሪዎቹን ግቦች ደግሞ ዚንቸንኮ፣ ፎደን፣ ወከርና ማኅሬዝ በየስማቸው አስመዝግበዋል፡፡

በመጀመሪያው 45 ደቂቃ አራት ግቦችን ያስቆጠሩት ሲቲዎች ቀሪዎቹን 5 ግቦች ደግሞ ከእረፍት መልስ አስገብተዋል፡፡

በካራባዎ ዋንጫ ማንቸስተር ሲቲ ከአለፉት አምስት ዓመታት ውድድሮች በሦስቱ ዋንጫውን ማንሳቱ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Previous articleአርቲስት መሀሪ ደገፋው ፋሲል ከነማን ለመደገፍ ዛሬ ቃል ገብቷል ፡፡ አርቲስቱ ሰሞኑን ከሚኖርበት አሜሪካ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል፡፡
Next articleአጼዎቹ በመቀሌ ኤርፖርት በወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፤ በመቀሌ 70 እንደርታ ደጋፊዎች እና የክለብ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።