ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የእስራኤልን አምባሳደር አነጋገሩ፡፡

238
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የእስራኤልን አምባሳደር አነጋገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በኢትዮጵያ የእስራኤልን አምባሳደር በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ነው የተወያዩት። ቅዱስነታቸው ከአምባሳደሩ ጋር በኢትዮጵያና በእስራኤል ዘመን የተሻገረ የእርስ በእርስ ግንኙነት ላይም መክረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በኢየሩሳሌም በሚገኙ የኢትዮጵያ ገዳማት ዙርያ ያሉ ችግሮችን ለመፍታትም ተወያይተዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየ‹‹ዓለም ባንክ ግሩፕ›› ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ በክልሉ በሚገኙ 32 ከተሞች የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አስታወቀ።
Next articleአጼ ቴወድሮስ ከቋራ እስከ መቅደላ የሠሩትን ታሪክና አካባቢውን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ።