በኢትዮጵያ አይሲቲ ተሰጥኦ ሥነ ምሕዳርን ለማልማት የሚረዳ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈረመ፡፡

241
በኢትዮጵያ አይሲቲ ተሰጥኦ ሥነ ምሕዳርን ለማልማት የሚረዳ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈረመ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና በቴሌኮም መሠረተ ልማት ዋና አቅራቢነት የሚታወቀው ሁዋዌይ በኢትዮጵያ አይሲቲ ተሰጥኦ ሥነ ምህዳርን ለማልማት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ ሥነ ምህዳሩ ተማሪዎች እና ባለሙያዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ማረጋገጫ እንዲያገኙ እና በቴሌኮም እና በአይቲ ዘርፍ የሚኖራችውን የወደፊት ጉዞ እንዲያዳብሩ የሚረዳ ነው።
ትብብሩ ሲተገበር የሁዋዌይ ሥልጠና እና የብቃት ማረጋገጫ አዳዲስ ተመራቂዎች ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ከማገዙም በላይ በኢንዱስትሪው ውስጥ ለሚገኙ ሥራ ፈጣሪዎች አዳዲስ ክህሎቶችን ያስታጥቃል፡፡ በኮሚሽኑ የክህሎት ማዳበር እና የሥራ ፈጠራዋች ክትትል እንዲሁም የሥራ ስምሪት መርሃግብሮች አማካኝነትም በሀገር ውስጥ ላለው የሥራ ኃይል ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዕውቅና ይሰጣል ነው የተባለው፡፡
ይህ የሥልጠና እና የብቃት ማረጋገጫ መርሃግብር ለሶስት ዓመታት የሚቀጥል ሲሆን በመጀመሪያው ዓመት ለ800፣ በሶስት ዓመታት ደግሞ ለ7 ሺህ ወጣቶች የብቃት ማረጋገጫ የሚሰጥ ሲሆን፤ ለ 3ሺህ ወጣቶች ሶስት ዓመታት በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ውስጥ የሥራ ዕድሎችን የማመቻቸት እቅድ የያዘ ነው።
በተጨማሪም በመጀመሪያ ዓመት 40 ዩኒቨርስቲዎች ላይ ግንዛቤን ለማሳደግ፣ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ ሥልጠናዎችን እና የማዕከሉን ተመራቂዎች ቁጥር ለማሳደግ ያለመ ሲሆን በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ደግሞ 100 ዩኒቨርስቲዎችን እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማትን ለመሸፈን ዓላማ ያረገ መሆኑን ከሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ሀብት ለማፍራት ብቻ ሳይሆን ያለውንም ለመጠበቅና ሕይወትን ለመታደግ የሠላም መኖር ወሳኝ ነው” ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
Next articleየ‹‹ዓለም ባንክ ግሩፕ›› ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ በክልሉ በሚገኙ 32 ከተሞች የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አስታወቀ።