
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አገኘሁ ተሻገር የረመዳን ጾምን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አገኘሁ ተሻገር 1 ሺህ 442ኛው ሂጅራ የረመዳን ጾምን አስመልክቶ ለእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም “ፆማችሁ የእዝነትና የበረከት ይሁንላችሁ” ብለዋ፡፡
የእስልምና ሃይማኖት ከተገነባባቸው መሰረቶች መካከል የረመዳን ጾም አንዱ ነው፡፡ በረመዳን ወር የሃይማኖቱ ተከታዮች ካላስፈላጊ ተግባራት በመራቅ ከፈጣሪያቸው ምህረት የሚፈልጉበት ወር ነው፡፡
ከሌላው ጊዜ በበለጠ ለተቸገሩ ወገኖች በማብላት፣ በማጠጣት፣ በመደጋገፍ እና በመተጋገዝ ጭምር የሚከበር የጾም ጊዜ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ