
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ አዲስ አወቃቀር ማውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡ ቡድኖችን 24 በማድረስ ለሁለት በመመደብ እንዲወዳደሩ ነው ሀሳብ ያቀረበው፡፡ ፌደሬሽኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ደግሞ የውድድሩ አሸናፊ የሚለይበትን መንገድ ይፋ አድርጓል፡፡
የፕሪሚዬር ሊጉ አሸናፊ የሚሆኑት የየምድቦቹ አሸናፊዎች ወይም አንደኛ ሆነው ያጠናቀቁ ቡድኖች በገለልተኛ ሜዳ ሁለት ዙር ጨዋታ አድርገው አሸናፊ የሆነው የፕሪሚዬር ሊጉ አሸናፊ ይሆናል ብሏል፡፡ አሸናፊው ቡድን ኢትዮጵያን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲወክል ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ደግሞ በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ይወክላል፡፡
የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አሸናፊ የሆነው ደግሞ ኢትዮጵያን በሴካፋ እንደሚወክል ተገልጧል፡፡ የሊጉ መከፈልን ተከትሎ የሚፈጠረውን የጨዋታ መቀነስ ለማስተካከል ሦስተኛ የውድድር መርሀ ግብር ለማዘጋጀት እንደታሰበም ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል፡፡