“የረመዳን ጾም የበረካ ወር በመሆኑ በፍቅር፣ በመተሳሰብ እና በመተዛዘን ማሳለፍ ይገባል” ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ

395

“የረመዳን ጾም የበረካ ወር በመሆኑ በፍቅር፣ በመተሳሰብ እና በመተዛዘን ማሳለፍ ይገባል” ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ
ሐጂ ዑመር እድሪስ በሰጡት መግለጫ በየቦታዉ ያለዉ ግድያ መቆም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የሃይማኖት አባቶች በመተባበር ሕዝቡን ማስተማር እንደሚገባቸው እና መንግሥትም ኀላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ “ረመዳን ጾም የበረካ ወር በመሆኑ በፍቅር፣ በመተሳሰብ እና በመተዛዘን ማሳለፍ ይገባል”
ነው ያሉት፡፡
ለአንድነት እና ለሠላም ሁሉም ኀላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
በጾሙ ወቅትም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ታሳቢ ያደረገ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል፡፡ ከወንጀል እና
ከበደል በመቆጠብ ከአምላክ ጋር መታረቅና መቅረብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ጽዮን አበበ-ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article‹‹የኢንዱስትሪ መንደር መጠንሰሻዋ ከተማ ትኩረት ትሻለች››
Next articleየባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ በግብር አሰባሰብ አርአያ ለሆኑ ነጋዴዎችና ተቋማት ዕውቅና ሰጠ፡፡