አምባሳደር ተፈሪ መለሰ የቋሚ መልእክተኛነት የሹመት ደብዳቤ ለዓለም አቀፉ ማሪታየም ድርጅት ዋና ጸሐፊ አቀረቡ፡፡

160

አምባሳደር ተፈሪ መለሰ የቋሚ መልእክተኛነት የሹመት ደብዳቤ ለዓለም አቀፉ ማሪታየም ድርጅት ዋና ጸሐፊ አቀረቡ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) መቀመጫውን ለንደን ያደረገውና ኢትዮጵያ ከ1975 (እ.አ.አ) ጀምሮ አባል
ለሆነችበት ዓለም አቀፉ ማሪታየም ድርጅት ዋና ጸሐፊ ኪታክ ሊም የሹመት ደብዳቤያቸውን ዛሬ ያቀረቡት አምባሳደር ተፈሪ በስነ
ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት የማሪታየም ኢንዱስትሪ ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብታዊ እድገት ከፍተኛውን ሚና በመጫወት ላይይገኛል
ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ብትሆንም 11 የእቃ ማጓጓዣ መርከቦች እና የስምንት ደረቅ ወደቦች ባለቤት መሆኗን ለዋና9 ጸሐፊው
አስረድተዋል ፡፡
አክለውም ከስድስት ሺህ በላይ የመርከብ ሠራተኞች
ያሏት ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ቀንድ ለገቢና ወጪ ንግድ የማሪታየም ኢንዱስትሪዋ ማደግ ወሳኝ አስተዋጽኦ እንዳለው
ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የማሪታየም ኢንዱስትሪዋን አገልግሎት ዘመናዊ ለማድረግ አዳዲስ የሎጅስቲክስ መሰረተልማት ዝርጋታዎች
መካሄዳችውን አውስተው ይህም ለማሪታየም ኢንዱስትሪ እድገት እንቅፋት የሆኑ ማነቆዎችን በማስወገድ የዘርፉን እድገት
እያፋጠነ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
አለም አቀፉ የማሪታየም ድርጅት ያወጣቸውን የአሠራር መስፈርቶች በማሟላት በተለይም ኢንዱስትሪው
የሚከተለውን የሰማያዊ ውኃ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ መርህ በመከተል ዘርፉ የውኃ አካባቢ ደኅንነትን ሳይጎዳ ቀጣይነት ያለው
የማሪታየም እድገትን ለማፋጠን መቻሉን አምባሳደር ተፈሪ ተናግረዋል ፡፡
ኢትዮጵያ በማሪታየም ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ኀይልና ዘመናዊ መርከቦችን በመጠቀም ኢንዱስትሪው ይበልጥ
ውጤታማ እንዲሆን እያደረገች መሆኗን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ማሪታየም ኢንስቲትዩት ከባሕርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከፍተኛ ባለሙያዎችን በብቃት እና ጥራት በማሰልጠን
ለኢትዮጵያ ማሪታየም እና ለዓለም አቀፉ የማሪታየም ኢንዱስትሪ እድገት አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
አያይዘውም በኢትዮጵያ የሚገኘው የባሕርተኞች ማሰልጠኛ ዩኒቨርሲቲ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ከዓለም አቀፉ ማሪታየም
ድርጅት ድጋፍ እንዲደረግለት ጠይቀዋል፡፡ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን በሙሉ አቅም ለመፈጸም ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ድርጅቱ
በማቴሪያል እና በቴክኒክ እንዲደግፍም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኤምባሲው ከዓለም አቀፉ የማሪታየም ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት ምንጊዜም ዝግጁ መሆኑን አምባሳደር ተፈሪ አረጋግጠዋል።
የዓለም አቀፉ ማሪታየም ድርጅት ዋና ጸሐፊ ኪታክ ሊም በበኩላችው በዓለማችን ላይ ካለራሳቸው የወደብ
ባለቤትነት ታላላቅ የመርከብ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ሀገራት መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፉ ማሪታየም አባል ሀገራት ተወዳዳሪ የሰለጠነ የሰው ኀይል በማቅረብ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተች መሆኗን
አስታውሰዋል፡፡
ድርጅቱ በስዊዲን እና ማልታ ባሉት ዓለም አቀፍ የማሪታየም ባለሙያተኞች እና የማሪታየም ሕግ ማሰልጠኛ አማካይነት
የኢትዮጵያ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ማሪታየም ድርጅት የሚፈልጋቸውን የቴክኒክ የሙያ እና የማቴሪያል ድጋፍ
በማድረግ በማሪታየም አቅም ግንባታ ዘርፍ ሙሉ ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ምንጭ:- የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከለንደን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየአዉሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
Next article‹‹የኢንዱስትሪ መንደር መጠንሰሻዋ ከተማ ትኩረት ትሻለች››