“ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት በኩል የሚደረገው ድርድር እንዲቀጥል ጽኑ ፍላጎት አላት” ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ

223
“ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት በኩል የሚደረገው ድርድር እንዲቀጥል ጽኑ ፍላጎት አላት” ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት በኩል የሚደረገው ድርድር እንዲቀጥል ጽኑ ፍላጎት እንዳላት የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለጹ።
የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶክተር) በአፍሪካ ሕብረት በኩል በኮንጎ ኪንሻሳ የተደረገውን የሦስትዮሽ ድርድር በሚመለከት ዛሬ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ኢትዮጵያ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር በአፍሪካ ሕብረት በኩል እንዲቀጥል ጽኑ ፍላጎት እንዳላት አመላክተዋል።
በታዛቢነት የሚሳተፉ አካላት የአደራዳሪነት ሚና እንዲኖራቸው ግብጽና ሱዳን ያቀረቡትን ሃሳብ ኢትዮጵያ ውድቅ ማድረጓን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት በሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር አሜሪካ፣ የአውሮፓ ሕብረትና ደቡብ አፍሪካ በታዛቢነት እየተሳተፉ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ግድቡ ድርድር ላይ እነዚህ በታዛቢነት የሚሳተፉ አካላት ከታዛቢነት ባለፈ የአደራዳሪነት ሚና እንዲኖራቸው ግብጽና ሱዳን ሃሳብ ማቅረባቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ በድርድሩ ግብጽና ሱዳን ተጨማሪ ታዛቢ እንዲገባና ያሉትን የታዛቢዎች ሚና ለመቀየር ያሳዩትን ፍላጎት ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው በማሳወቅ ውድቅ አድርጋዋለች ብለዋል።
ግብጽና ሱዳን በተለይም ደቡብ አፍሪካን ከታዛቢነት ለማስወጣት ያደረጉትን ጥረትም መቃወሟን ጠቅሰዋል። ታዛቢዎቹ በድርድሩ ጣልቃ ሳይገቡ የታዛቢነት ሚናቸውን ለሁሉም ተደራዳሪዎች ጠቃሚ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ሦስቱ ሀገሮች እንደተስማሙ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
“ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት በኩል የሚደረገው ድርድር እንዲቀጥል ጽኑ ፍላጎት አላት” ብለዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ተፎካካሪ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙኃን የተመደበላቸውን የአየር ሰዓት በአግባቡ ሊጠቀሙበት ይገባል” የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ
Next articleበአማራ ክልል ለሥራ ዕድል ፈጠራ የተሰራጨውን የተዘዋዋሪ ብድር የመለሱ ወረዳዎች 41 ብቻ መሆናቸውን የአማራ ክልል ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡