የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ኢዜማ ለአዲስ አበባ ከተማ ያዘጋጀውን መሪ ዕቅድ ይፋ አደረገ።

243
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ኢዜማ ለአዲስ አበባ ከተማ ያዘጋጀውን መሪ ዕቅድ ይፋ አደረገ።
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ “እንደ ፓርቲ ሁሉም በሚመስሉትና በሚወክሉት መመራት አለበት ብለን ባዘጋጀነው መሰረት ለአዲስ አበባ በእጩነት ያዘጋጀናቸው አካላት 138 የአዲስ አበባ መሪ እቅድ አዘጋጅተዋል” ብለዋል።
በመልካም አስተዳደር፣ በሰላምና ደኀንነት፣ በመሰረተ ልማት፣ በሥራ እድል ፈጠራ፣ በመኖሪያ ቤት አቅርቦትና ኑሮ ውድነት፣ በዘመናዊ መሬት አስተዳደር፣ በማኀበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ዝመናና መሰል የማኀበረሰባዊና የኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በማሻሻል ላይ መሪ እቅዱ እንደተዘጋጀም ገልጸዋል።
በአንድ ሀገር ሁሉን አንድ ጊዜ ማሟላት ስለማይቻል ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ምንድንነው? ሕዝቡ አሁን ላይ ምን ይፈልጋል? በሚል የተዘጋጀ መሪ እቅድ ነው ብለዋል። ኢዜማም ከተመረጠ እነዚህን ትልሞች እውን እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
በከተማዋ እጅግ የበዙ ችግሮች መኖራቸውን ገምግመናል ያሉት ፕሮፌሰሩ ኢዜማ ከነዚህ ችግሮች ቅድሚያ ለሰጣቸው መፍትሔ ይወስዳል ብለዋል።
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአማራ ክልል በጅምር የቀሩ የንጹህ መጠጥ ውኃ ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ውኃ፣መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
Next articleበባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር እየተገነባ ያለው የዓባይ ድልድይ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የድልድዩ ምክትል ተጠሪ መሀንዲስ ገለጹ፡፡