
ባሕር ዳር፡ ታኅሳስ 24/2011ዓ.ም (አብመድ) አርቲስት መሀሪ ደገፋው ፋሲል ከነማን ለመደገፍ ዛሬ ቃል ገብቷል ፡፡
አርቲስቱ ሰሞኑን ከሚኖርበት አሜሪካ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል፡፡

ፋሲል ከነማን ለመደገፍም ቅዳሜ በጎንደር በሚደረግ ኮንሰርት አንዱን ትኬት በ50 ሺህ ብር በመግዛት ለክለቡ ገቢ እንደሚያደርግ ተናግሯል፡፡ ክለቡን ለመደገፍ ከሚሰራ ማንኛውም አካል ጋር በመሆን እንደሚሰራም ገልጿል፡፡
አርቲስት መሀሪ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ ከአርቲስት ይሁኔ በላይ ጋር በመሆን ፍቅር ያሸንፋል ኮንሰርትን በተለያዩ ከተሞች ያካሂዳል፡፡ ኮንሰርቱም የፊታችን ቅዳሜ በጎንደር ይጀምራል፡፡
ዘጋቢ፡-ንዋይ ሙሉጌታ