
በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ ከተማ የተካሄደው የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ሩጫ በሰላም ተጠናቋል፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 26/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን የደጋፊዎች ማኅበር ያዘጋጀው የሩጫ ውድድር ድርብ ዓለማ የነበረው መሆኑን የደጋፊ ማኅበሩ አስታውቋል፡፡
የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ማኅበር ሊቀ መንበር ኃይለማርያም ፈረደ በወልቃይት ጠገዴ ዳንሻ ከተማ የተካሄደው የሩጫ ውድድር ስኬታማ እንደነበር ተናግሯል፡፡ ሩጫው ለፋሲል ከነማ ከገቢ ማስገኛ በላይ ነው ያለው ሊቀመንበሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በነጻነት ክለባቸውን የደገፉበት ነበርም ብሏል፡፡
ከአሁን ቀደም የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ነዋሪዎች የፋሲል ከነማን እግር ኳስ ቡድን መለያ አደረጋችሁ በሚል ሰበብ ብቻ ለእስር እና ለእንግልት ሲዳረጉ እንደነበር ይታወሳል፡፡
በዳንሻ ከተማ የተካሄደው የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን “ከክለብም በላይ” ሩጫ በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ ያሳለፈውን የአካባቢው ማኅበረሰብ ያስደሰተ እንደነበርም የደጋፊ ማኅበሩ ሊቀመንበር ተናግሯል፡፡
በሩጫው የውልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ማኅበር የእግር ኳስ ቡድኑን በገንዘብ ለመደገፍና የደጋፊዎችን ቁጥር ለመጨመር የሚያደረገው ሩጫ በሌሎች ከተሞች እንደሚቀጥሉም ሊቀመንበሩ አስታውቋል፡፡
ገንዳ ውኃ፣ ደባርቅና ደብረታቦር ከተሞችም ቀጣይ የፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ቡድን ታላቁ ሩጫ ይካሄድባቸዋል ተብሏል፡፡
በዳንሻ የሚገኜው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአማራ ሚሊሻ የአካባው አስተዳደርና በጎ አድራጊ ወጣቶች ሩጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ማድረጋቸውንም አስታውቋል፡፡
በዳንሻ የተካሄደው የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ከክለብ በላይ ሩጫ በስኬት መጠናቀቁንም ተናግሯል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ፎቶ: ከደጋፊ ማኀበሩ




ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ