አብቁተ አይቻልም የሚባለውን መንፈስ የቀየረ ተቋም መሆኑን አቶ ገዱ እንዳርጋቸው ተናገሩ፡፡

370
አብቁተ አይቻልም የሚባለውን መንፈስ የቀየረ ተቋም መሆኑን አቶ ገዱ እንዳርጋቸው ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) ወደ ፀደይ ባንክ ሽግግር የባለ አክሲዮኖች ጉባኤ በባሕርዳር እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባኤው ላይ የተገኙት የአብቁተ የሥራ አመራር ቦርድ ሊቀመንበርና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ከአብቁተ ለችግር መፍትሔ ማምጣት ትምህርት ይገኛል ብለዋል፡፡ ከመጠበቅ ይልቅ፣ ከራስ የመፈለግ እሳቤ ምን ያክል ኃያል እንደሆነ ሁሉም ሊማርበት የሚገባ ነው፣ ይህንም አብቁተ አሳይቷል ነው ያሉት፡፡
አብቁተ ሲመሠረት የክልሉ ሕዝብ በችግር ውስጥ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ገዱ በወቅቱ ከነበረው ሕዝብ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ከድኅነት ወለል በታች ነበር፤ ይህ ችግር እያለ አማራ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ነው የሚሉ ፖለቲከኞች እንደነበሩ ጠቅሰዋል፡፡ በወቅቱ ብድር መበደርና ተበድሮ ሠርቶ የመመለስ ፍላጎት እንዳልነበርም ያስታወሱት አቶ ገዱ ለአብቁተ ችግር እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
ለብድር የሚሆን ገንዘብ ከዬት ይመጣል የሚል አስተሳሰብም ነበር ነው ያሉት፡፡
አብቁተ ድሆችን ለመደገፍ የተቋቋመ መሆኑን ያነሱት አቶ ገዱ ድሆች ሠርተው መመለስ ይችላሉ በሚል ለድሆች በመስጠት የድሆችን ኑሮ በመሻሻል ታላቅ ተቋም ሆኗል ነው ያሉት፡፡
ተቋሙ የይቻላል መንፈስን ያሳዬ ነውም ብለዋል፡፡ የችግር መፍትሔን ከራስ መፈለግ እንደሚገባም የተናሩት አቶ ገዱ አብቁተ በሂደቱ የቀረፈው የገንዘብ ችግር ብቻ ሳይሆን አይቻልም የሚለውን መንፈስም ነው ብለዋል፡፡
አብቁተ ታማኝና ታታሪ ሠራተኞችን ማፍለቂያ ሆኗልም ነው ያሉት፡፡ አብቁተ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የብድር ደንበኞችን በመያዝ የቀዳሚነት ደረጃን ይዞ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡ ከ8 ሚሊዮን በላይ የክልሉ ነዋሪዎችም የቁጠባ ደንበኛ ሆኗል ብለዋል፡፡ 9 ነጥብ 2 ቢሊዮን ካፒታልና 36 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ሀብት ያለው ተቋም መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አብቁተ በክልሉ ውስጥ ዋነኛ አበዳሪ የልማት ክንድ ሆኗልም ነው ያሉት፡፡ ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ ላደረጉት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ አብቁተ ክልሉን የበለጠ የልማት ደጋፊ ለመሆን፣ ተወዳዳሪ ለመሆንና አብቁተን ከማይክሮ ፋይናንስ አደጋ ለማዳን ሲባል ወደ ባንክ ማደግ እንዳስፈለገም ተናግረዋል፡፡ ለአብቁተ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleʺእንደ ነበረ አይኖር ሁሉም ይለወጣል : የእነርሱ ቀን ሲመሽ ያንተ ቀን ይወጣል…”
Next article“አብቁተ በክልሉ ሥር የሰደደ ድህነትን ለመዋጋትና ልማትን እውን ለማድረግ የተመሠረተ የፋይናንስ ተቋም ነው” የአብቁተ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መኮንን የለውምወሰን