በደሴ ከተማ 115 ሺህ 300 ሀሰተኛ የብር ኖት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

222

በደሴ ከተማ 115 ሺህ 300 ሀሰተኛ የብር ኖት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 24/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የ2ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የኮምዩኒኬሽንና ሚዲያ
ክፍል ኀላፊ ኢንስፔክተር እስከዳር ካሳዬ እንደገለጹት መጋቢት 23/2013 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት አካባቢ ተጠርጣሪ ጌትነት
መኩሪያ በደሴ ከተማ ቀበሌ 06 በሚገኝ ለማረፊያ ከተከራየበት አልጋ ቤት ውስጥ ያስቀመጠው 115 ሺህ 300 ሀሰተኛ የብር
ኖት በአልጋ ቤቱ ባለቤት ጠቋሚነትና በኅብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ተጠርጣሪው በተከራየው አልጋ ቤት ካስቀመጠው ሀሰተኛ የብር ኖት በተጨማሪ በእጁ ይዞ እየተገበያየ እያለ በቁጥጥር ስር
እንደዋለ ተናግረዋል፡፡
በቁጥጥር ስር የዋለው ሀሰተኛ የብር ኖት 109 ሺህ 200 ብር ባለ ሁለት መቶ የብር ኖት እና 6 ሺህ 100 ብር ባለ አንድ መቶ
የብር ኖት ነው፡፡ ኅብረተሰቡም ሲገበያይ በሀሰተኛ የብር ኖቶች እንዳይጭበረበር ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ኢንስፔክተር
እስከዳር መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ጀማል ሰይድ – ከደሴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበኃይል ተሸካሚ ምሰሶ ላይ በደረሰ ስርቆት ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
Next article“…የድሃ ሞት እና ጭፍጨፋ እንዲሁም ያልተረጋጋች ሃገር መፍጠር የእርካታ ምንጫቸውና መኖሪያቸው ያደረጉ ኃይሎችን ያለምህረት የመታገል እንዲሁም በየደረጃው ኃላፊነታቸውን የማይወጡ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን