በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

656

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 22/2013 ዓ.ም (አብመድ) ጥቃቱ የተፈጸመው በዞኑ ማንዱራ ወረዳ ጂግዳ ቀበሌ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ ሲጓዝ በነበረ መለስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ተጓዦችን በማስወረድ ግድያ ተፈጽሟል፡፡ የቆሰሉት ደግሞ ወደ ፓዊ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡

በጥቃቱ የሞቱ ፣ የቆሰሉ እና ታግተው የተወሰዱትን ሰዎች ቁጥር ግን በትክክል እንደማያውቁ ነው የገለጹት፡፡ ወደ ቻግኒ እና ወደ ግልገል በለስ የተሽከሪካሪ እንቅስቃሴ መቆሙንም ተናግረዋል፡፡

በወረዳው በገነተ ማርያም ቀበሌ በተመሳሳይ የታጠቁ ቡድኖች በነዋሪዎች ላይ የከፈቱትን ተኩስ ግን የአካባቢው የፌዴራል ፖሊስ እና የሀገር መከላከያ ስራዊት መከላከል መቻላቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ አሁንም በገነተ ማርያም ቀበሌ ላይ የተኩስ ድምጽ እንዳለ ጠቅሰዋል፡፡

አብመድ አካባቢውን ለሚመራው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ በጉዳዩ ላይ መረጃ ለመጠየቅ ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ቀጠሮ አስይዞ በሰዓቱ በእጅ ስልካቸው በተደጋጋሚ ቢደወልም ባለመነሳቱ ሃሳባቸውን ማካተት አልቻለም፡፡ እንዳገኘናቸው ምላሻቸውን የምናካትት ይሆናል፡፡

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ

Previous articleየፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
Next articleየክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ሕዝቡን እንዲያወያዩና ጥፋተኞችም በሕግ እንዲጠየቁ የከሚሴ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡