
በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ገዳማት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአስር ሺህ የአሜሪካን ዶላር የቦንድ ግዢ ፈጸመች፡፡
ባሕር ዳር: መጋቢት 22/2013 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አባ ዕንባቆም እንዳሉት “ሀገራችን ያላትን የተፈጥሮ ፀጋ መጠቀም አስፈላጊ ነው።”
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ ቤተክርስቲያኗ ድጋፏን እንደምትቀጥልም ገልጸዋል፡፡
“የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ በጨለማ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖቻችን ብርሃን ይሰጥ ዘንድ፣ ሁሉም አቅሙ የፈቀደውን ድጋፍ ያድርግ” ብለዋል ብጹዕነታቸው።
በእስራኤል የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አምባሳደር ረታ ዓለሙ ለድጋፉ የገዳሙን አባቶች አመስግነዋል።
በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ አምባሳደሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በገዳማቱ ውስጥ የሚገኙ መነኮሳት በቀጣይ በግላቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ መግለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ