
በሲያትል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን አሜሪካ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በአግባቡ አንድትመለከት ጠየቁ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 18/2013 ዓ.ም (አብመድ) በአሜሪካ ሲያትል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ሰላማዊ ሰልፍ
አድርገዋል። በሰልፉ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የሕወሓት ተላላኪዎች በክፍያ እየሰሩት ያለውን ፕሮፓጋንዳ
አውግዘው፤ ሁለቱ የአሜሪካ ምክር ቤቶች የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በአግባቡ እንዲመለከቱት ጠይቀዋል።
ሰላማዊ ሰልፉን ያስተባበሩት የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቲም እና አለን ለአባይ ከቅንጅት የኢትዮጵያ ሴቶች በሲያትል ጋር
በመተባበር ነው። ሰልፈኞቹ ሕወሓት በጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ላይ የፈጸመውን የሀገር
ክህደት ወንጀልም አውግዘዋል።
በውጭ ያሉ የሕወሓት ሰዎች ባለፉት 30 ዓመታት ከኢትዮጵያ ህዝብ በዘረፉት ገንዘብ የሎቢ ቡድኖችን በመቅጠር የኢትዮጵያን
ስም ለማጠልሸት እና የዲፕሎማሲ ጫና ለመፍጠር እየሰሩ እንደሚገኙ የሰልፉ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
ሰልፈኞቹ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ እየተካሄደ ያለውን የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲገነዘበው ለማድረግ 12 ገጽ
የአቋም መግለጫ አውጥተው ለሚመለከታቸው አካላት አሰራጭተዋል።
መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m