
“የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ሀገርን ከመበተን የታደገ፣ ዘመን የማይሽረው ታሪካዊ ተጋድሎ የፈጸመ ነው” የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 17/2013 ዓ.ም (አብመድ) የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወልደትንሳኤ መኮንን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የጁንታው ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ክህደትና ጥቃት ሲፈፅም ቀድሞ በመገኘት በሀገር ህልውና እና በሠራዊቱ ላይ የተቃጣውን ሀገርን የማፈራረስ አጀንዳ ፊት ለፊት ደረቱን እና ህይወቱን በመስጠት መስዋእትነት የከፈለ ነው ብለዋል፡፡
ልዩ ኀይሉ ከከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት ጁንታው ወደ መቃብር እንዲወርድ ያደረገ ዕንቁ የጸጥታ ኃይል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው ይህን አኩሪ ተጋድሎ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቀው ጥሬ ሀቅ አንደሆነም ተናግዋል፡፡
ይሁን እንጂ ሰሞኑን በአንዳንድ የውስጥና የውጭ ኃይሎች በተሳሳተ ሁኔታ በልዩ ኃይሉና በሚሊሻው ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ እየተካሄደ ነው፤ ከዚህ የስም ማጥፋት ዘመቻ መረዳት የሚቻለው ልዩ ኃይሉም ሆነ ሚሊሻው በመስዋእትነት የፈፀሙትን አኩሪ ገድልና ሀገርን የማዳን ተልዕኮ ጥላሸት ለመቀባት ታልሞ የተደረገ ነውረኛ ድርጊትና ዘመቻ ነው ብለዋል፡፡
የአማራ ልዩ ኃይል ከክልሉ አብራክ የተገኘ ስሪቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ፣ ዛሬም ሆነ ነገ ለቆመለት ዓላማ የማይበገር፣ ማዕበልና ወጀብ የማያናውጠው በፅኑ መሠረት ላይ የተገናባ ህዝባዊ መሠረት ያለው መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡
አቶ ወልደትንሳኤ መኮንን “በጥላቻ የሚደረጉ የሀሰት ውንጀላዎች እንደ ብረት ምሰሶ ያጠነክሩት እንደሆነ እንጂ ከቆመለት ዓለማ ወደ ኋላ የሚመልሰው አንዳች ነገር አይኖርም” ብለዋል፡፡ መረጃው የሰሜን ወሎ ዞን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ