የትህነግ ርዝራዦችን በንቃት እየጠበቀ መሆኑን የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

333

የትህነግ ርዝራዦችን በንቃት እየጠበቀ መሆኑን የዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ጥቃት ያደረሰውን የትህነግን ቅሬት በመደምሰስና በመበተን አካባቢውን ሰላም ማድረግ መቻሉንም ብሔረሰብ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 15/2013 ዓ.ም (አብመድ) በየሰርጡ የተበነው የትህነግ ቅሬት ቡድን መጋቢት 09/2013 ዓ.ም በአማራ ክልል ዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በጻታ ወረዳ በንጹሃን ዜጎችና በንብረት ላይ ጥቃት አድርሷል፡፡

ርዝራዥ ቡድኑ ከዚህም በከፋ በብሔረሰብ አስተዳደሩ ጥቃት በማድረስ ንጹሃንን ለመጨፍጨፍ ቢያስብም የብሔረሰብ አስተዳደሩ ሚሊሻ ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ ርዝራዥ ቡድኑን በመመከት ያሰበውን እንዳያሳካ አድርጓል፡፡

ቀን ጠብቆ ለዘረፍና ለመግደል የመጣውን እኩይ የትህነግ ርዝራዥ የፀጥታ ኃይሉ ብቻ ሳይሆን የአካባቢው ማኅበረሰብ እጁ ላይ ባገኘው መሳሪያ እየተከላከለ፣ እየመለሰና እያጠቃ ከጉዞው ገትቶታል፣ ከዓላማው አሰናክሎታል፣ ህልሙንም ባዶ አስቀርቶታል፡፡ ማኅበረሰቡ ባደረገው ተጋድሎ የመጣውን በደረሰበት እንዲቀር አድርጎታል፤ የማኅበረሰቡ በልበ ሙሉነት መዋደቅ የከፋውን ኪሰራ አምክኖታል፡፡ የጻታና አካባቢው ነዋሪ አስቦና በመሳሪያ ትጥቅ ተሞልቶ የመጣውን አጥፊ ቡድን እንደ ለመደው አንዲሸነፍ፣ እንዲበተን እና እንዲደመሰስ አድርጎታል፡፡

ተጋድሎ ያደረገው የሚሊሻ ኃይሉ ለጥፋት የመጣውን ቡድን በመደምሰስና ከፊሉንም በታትኖታል፡፡ ከሚሊሻው ተጋድሎ በተጨማሪ የአማራ ልዩ ኃይልና የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወደ ስፍራው በማቅናት ቡድኑ ላይ እርምጃ ወስዷል፡፡

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ተዋካይ አስተዳዳሪ ኃይሌ አምሳሉ ለአብመድ እንደተናገሩት የአካባቢው ማኅበረሰብ ከሚሊሻው ጋር በመተባበር አስደናቂ ተጋድሎ አድርጓል፡፡ በነበረው ድንገተኛ ጥቃት ሕዝባዊ ፖሊስን ጨምሮ የነበረው የፀጥታ ኃይል የርዥራዡን ሀሳብ አክሽፈውታል ነው ያሉት፡፡

የፀጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃም የትህነግ ርዝራዥ በሰውና በንብረት ላይ ሊያደርሰው የነበውን የከፋ ጉዳት ማክሸፉንም ተናግረዋል፡፡ ብሔረሰብ አስተዳደሩ ከክልሉና ከፌዴራል የፀጥታ ኃይል ጋር በመቀናጀት የጸጥታውን ሁኔታ በንቃት እየጠበቀ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ማኅበረሰቡም በጠንካራ ሥነ ልቦናና ወኔ ላይ ሆኖ አካባቢውን እየጠበቀ ቢሆንም፣ አሁንም በየ ጥሻው ያለው የትህነግ ርዝራዥ ከዘረፋ ተግባሩ ስለማይቆጠብ የተጠናከረ የጸጥታ ሥራ እንደሚያስፈልግ የጻታ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

አካባቢውን በንቃት የሚጠብቅ ኃይል መደራጀቱን የብሔረሰብ አስተዳደሩ የሰላምና ደኅንነት መምሪያ ምክትል ኃላፊ 50 አለቃ አዘዘው አዳነ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ከፍያለው ደባሽ – ከሰቆጣ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበአንኮበር ወረዳ የወፍ ዋሻ ተብሎ በሚጠራው ደን ላይ የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ለመቆጣጠር ከአቅም በላይ እንደሆነበት የወረዳው አስተዳደር ገለጸ፡፡
Next articleዘመን ገፋት ዘመን ደገፋት – የጣና ዳሯን እመቤት፡፡