በሳምንቱ ከሳኡዲ አረቢያና ከየመን ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

114
በሳምንቱ ከሳኡዲ አረቢያና ከየመን ከ1 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 14/2013 ዓ.ም (አብመድ) በሴናተር ክሪስ ኩዊንስ የተመራ የአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ልኡካን በኢትዮጵያ ባደረገው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ጋር ውይይት ማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል፡፡
ለሴናተር ክሪስ ኩዊንስ እና ልኡካቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እና ወደፊትም መኖር ስለሚገባው ጉዳይ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል፡፡ አሜሪካም በትግራይ ክልል የሚደረገውን ድጋፍ ትኩረት እንድትሰጥ ለሴናተሩ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል፡፡
ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር በነበራቸው ቆይታም የሀገሪቱን ሰላም በማስከበር ዙሪያ እንዲሁም ኢትዮጵያ ጣልቃ ገብነት አንደማትቀበል ገለጻ ተደርጎላቸዋል ነው ያሉት፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰላም ማስከበር ላይ እያደረገች ያለውን አስታውጽዖ ማስገንዘባቸውን ጠቅሰዋል፡፡
የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሸነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በበኩላቸው በትግራይ ክልል እየተከናወነ ስላለው ሰብዓዊ ድጋፍ ማብራሪያ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡ ልኡኩ በጉዳዩ ላይ በቂ ማብራሪያ አንዳገኘ እና በቀጣይም ለመንግሥታቸው የሚያቀርቡት ሪፖርት ይጠበቃል ብለዋል፡፡
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሳምንቱ ከሳኡዲ አረቢያ 1 ሺህ 283 ከየመን 143 ዜጎችን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል ፡፡
ዘጋቢ፡- አንዱአለም መናን – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleከሕግ ማስከበር ዘመቻ በኋላ 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎችን መመገብ እንደታቸለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) ተናገሩ፡፡
Next article“የአማራ ልዩ ኃይል በሕግ ማስከበር ዘመቻው መሬቴን ላስመልስ ብሎ ተደራጅቶ ወደ ዘመቻው እንደገባ የሚያስመስሉ አሉ፣ ይህ ስህተት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር)