በስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ በአካባቢው ኅብረተሰብ ተሳትፎ ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን የፓርኩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

510

በስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የተከሰተውን የእሳት ቃጠሎ በአካባቢው ኅብረተሰብ ተሳትፎ ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ
መሆኑን የፓርኩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 12/2013 ዓ.ም (አብመድ) በስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ጅንባር ፏፏቴ፣ ሻይኖና ባርና እና ቧይት
አካባቢ ልዩ ስሙ አማራ ሸማ ተብሎ በሚጠራው ገደላማ የፓርኩ ክፍል የእሳት ቃጠሎ መከሰቱን የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ
ፓርክ ጽሕፈት ቤት የማኅበረሰብ እና ቱሪዝም ኀላፊ አቶ ታደሰ ይግዛው አስታውቀዋል፡፡ ኀላፊው እንደነገሩን እሳቱ መጋቢት
11/2013 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 በኋላ ነበር የተከሰተው።
እንደ ኀላፊው ገለፃ የአደጋው መንስኤ አልታወቀም። የእሳት ቃጠሎው መከሰቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶም የፓርኩ ሠራተኞች፣
የሥራ ኀላፊዎች እና የአካባቢው አርሶ አደሮች ክስተቱን ለመቆጣጠር ወደ ቦታው አምርተዋል። ጅንባር ፏፏቴ፣ ሻይኖና ባርና
በሚባሉ የፓርኩ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውን የእሳት ቃጠሎ ወዲያውኑ መቆጣጠር መቻሉን አቶ ታደሰ ተናግረዋል።
ቧይት አካባቢ ልዩ ስሙ አማራ ሸማ ተብሎ በሚጠራው ገደላማ የፓርኩ ክፍል የተከሰተውን የእሳት አደጋ በአካባቢው
ማኅበረሰብ እና በፓርኩ ሠራተኞች አቅም መቆጣጠር እንደሚቻል እና ርብርብ እያደረጉ መሆኑን ነግረውናል፡፡
ቃጠሎው ቀላል መሆኑን እና ገደላማ የፓርኩ ክፍል የተከሰተውን ዛሬ መቆጣጠር እንደሚቻል ነው ኀላፊው ያስታወቁት፡፡
በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ የብርቅየ አራዊት መገኛ የሆነው የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ከአሁን በፊትም ተመሳሳይ አደጋ
ገጥሞት እንደነበር ይታወሳል።
ዘጋቢ:- ሀይሉ ማሞ
ፎቶ፡ ከድረ ገጽ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙ ዘር ተኮር ጥቃቶች በአጥፊዎች ላይ ርምጃ በመውሰድ እንዲቆሙ አብን ጠየቀ።
Next article“የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 10ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል” የአማራ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት