
በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙ ዘር ተኮር ጥቃቶች በአጥፊዎች ላይ ርምጃ በመውሰድ እንዲቆሙ አብን
ጠየቀ።
ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባወጣው መግለጫ በሰሜን ሸዋ ዞን
በአጣዬና አጎራባች አካባቢዎች የጥላቻ ኃይሎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት በሕዝብ ላይ መክፈታቸውን እንዳረጋገጠ
አስታውቋል። በዚህም ምክንያት ሕይወት መጥፋቱን፣ አካል መጉደሉንና ንብረት መውደሙን አመላክቷል።
“ጥቃቱ የተከፈተውና እየተፈፀመ ያለው በመሀል የአማራ አካባቢዎች ሲሆን ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ሲፈፀሙ የነበሩ ጥቃቶች
ቀጣይ ክፍል ሆኖ በተለይ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ የትህነግን አሸባሪ ኃይል ለመመከት፣ ሕዝቡን፣ ክልሉንና ሀገሩን ለመከላከል
ወደ ክልሉ ምዕራባዊና ደቡባዊ ግዛቶች መንቀሳቀሱን ተከትሎ መሆኑ ብዙ ነገር ይገልጣል” ብሏል ፓርቲው።
ፓርቲው ቀደም ብሎ መረጃው በደረሰው ወቅት ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በማሳሰብ አጥፊዎቹ ጉዳት
ከማድረሳቸው በፊት አፋጣኝ እርምጃ ተወስዶ የሕዝብ ሰላም እንዲረጋገጥ ጠይቆ እንደነበርም ባወጣው መግለጫ
አስገንዝቧል።
“ጥቃቱ በተከፈተበትና በሌሎች ቅርበት ባላቸው አካባቢዎች የምትገኙ ወገኖቻችን በተለይም ወጣቶች የተለያዩ የጥፋት አጀንዳ
ባላቸው አካላት ሕዝቡን ለማሸበር ታስበው ከሚለቀቁ ሐሰተኛ መረጃዎች በመቆጠብ፣ ከመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጋር
በመተባበርና ውስጣዊ አንድነታችሁን በማጠናከር ለሕዝባችን ደኅንነት መረጋገጥ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ” በማለትም
አሳስቧል።
የአማራ ክልል መንግሥት የአመራሩን ውስጣዊ አንድነት ከመቸውም ጊዜ በላይ በማጠናከር፣ ለሰርጎ ገቦችና ሴረኞች እንዲሁም
ኢትዮጵያ እንዳትረጋጋ አበክረው የሚሰሩ የውጭ ኃይሎችና መገናኛ ብዙኃኖች በከፈቱት የተቀነባበረ ፕሮፖጋንዳና ወከባ
ሳይንበረከ፤ በሕዝቡ ላይ በየአቅጣጫው የተከፈተውን ዘር ተኮር ጥቃት በብቃት መመከት እንዲችልና ለዚህም ሁሉንም የአማራ
ኃይሎች ከጎኑ የማሰለፍ የማስተባበር ሚናውን በቁርጠኝነት እንዲወጣ አብን ጥሪ አቅርቧል።
በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙ ዘር ተኮር ጥቃቶችም በአጥፊዎች ላይ ርምጃ በመውሰድ እንዲቆሙ አብን
ጠይቋል። መንግሥት በአጥፊዎቹ ላይ የማያዳግም ርምጃ የማይወሰድ ከሆነ በቀጣይ ግንባር ቀደም የሀገር ኅልውናን አደጋ ላይ
የሚጥል ችግር መሆኑ እንደማይቀር ፓርቲው ባወጣው መግለጫ አስገንዝቧል።
ምንጭ: የአብን ማህበራዊ ትስስር ገጽ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m