
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ከሀገር ውስጥ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከ134 ሽህ በላይ
ታዛቢዎች እንደቀረቡ ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫን ለመታዘብ ፍላጎት ላላቸው የሀገር
ዉስጥ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ፍቃድ ለማግኘት ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ባወጣዉ ማስታወቂያ መሰረት 111 ድርጅቶች
እውቅናን ለማግኘት እንዳመለከቱ ገልጿል፡፡
ድርጅቶቹ ያቀረቡትን ማመልከቻዎች እና ተያያዥ ሰነዶች በምርጫ ሕጉ፣ በወጣዉ ጥሪ እና በመመሪያዉ የተደነገጉትን መስፈርቶች
እና ግዴታዎች ያሟሉ ስለመሆኑ፣ የድርጅቶቹ የማስፈፀም አቅም ተገምግሞ እና በየደረጃዉ የተጓደሉ ሰነዶችን እንዲያሟሉ
በማድረግ በመጀመሪያዉ ዙር ካመለከቱ ከ111 ድርጅቶች መካከል 43ቱ ድርጅቶች ወደ ሁለተኛዉ ዙር ካለፉ በኋላ 36ቱ
ስድስተኛዉን አጠቃላይ ምርጫ እንዲታዘቡ ተመርጠዋል ብሏል ቦርዱ፡፡
የተመረጡት 36ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች 134 ሽህ 109 ታዛቢዎችን ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
አስታውቋል፡፡
ከተመረጡ የሲቪል ማኅበራት ውስጥ
በሴቶች ጉዳይ ላይ በሚሰሩ 8 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የቀረቡ 61 ሽህ 851
ሴት ታዛቢዎች
በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ስር የታቀፉ 7 ማኅበራትን ያካተተ
244 ታዛቢዎች
በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የምርጫ ሂደትን ለመታዘብ በተመረጠ 1 የሲቪል ማኅበረሰብ
ድርጅት የቀረቡ 100 ታዛቢዎች እና
በስሩ 37 ያህል ሲቪል ማኅበራትን ያቀፈ የሲቪል ማኅበረሰብ ኔትወርክ ይገኙበታል።
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለተመረጡት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እንደሚያከናወን ገልጿል፡፡
የሚሠማሩ ታዛቢዎችን ለመደገፍ እና ለመከታተልም ስትራቴጂ መድነፉንም አመላክቷል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m