የመምህራንና የትምህርት ቤት የሥራ ኀላፊዎች ሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት የሚከታተል የሙያ ፈቃድ ምክር ቤት ሊመሰረት ነው።

526

የመምህራንና የትምህርት ቤት የሥራ ኀላፊዎች ሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት የሚከታተል የሙያ ፈቃድ ምክር ቤት ሊመሰረት
ነው።
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) የትምህርት ሚኒስቴር ለመምህራንና የትምህርት ቤት የሥራ ኀላፊዎች የሙያ
ፍቃድ አሰጣጥና እድሳትን የሚከታተል የሙያ ፍቃድ ምክር ቤት ለመመሰረት ውይይት እያካሄደ ነው።
“ለመምህራንና ለትምህርት የሥራ ኀላፊዎች የሙያ ፍቃድ መስጠትና ማደስ መምህሩንና የትምህርት አመራሩን በመማር
ማስተማሩ ሂደት ላይ ተግተው እንዲሠሩ ያስችላል” ብለዋል የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሁሪያ ዓሊ።
የሙያ ፍቃድ መስጠትና ማደስ ለትውልዱ ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ እንዲሆን የላቀ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ሚኒስትር
ዴኤታዋ ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዚደንት ዮሐንስ በንቲ (ዶክተር) በበኩላቸው የመምህራን ሙያ ፈቃድ አሰጣጥ በዓለም አቀፍ
ደረጃ መለኪያ ተቀምጦለት የሚከናወን እንደሆነና ውጤታማ የሆነ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ
እንደሚያበረክት መግለጻቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
በምክር ቤት ምስረታው ላይ የክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሥራ ኀላፊዎች፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር፣
የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዲኖች፣ የኢትዮጵያ የግል ትምህርት ቤቶች ማኅበር እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴር መሪዎችና
ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቦንድ ሳምንት ከመጋቢት 15 ጀምሮ ሊካሄድ ነው፡፡
Next articleየበጎ ፈቃደኛ አባላትን ቁጥር ለመጨመር እየሠራ መሆኑን በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር ሰሜን ምዕራብ አካባቢ ጽሕፈት ቤት ገለጸ፡፡