“በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ታሪክ እንደ 2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ብዙ ልጆቻችንን ያጣንበት ዓመት ታይቶ አይታወቅም፡፡” የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

725

“በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ታሪክ እንደ 2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ብዙ ልጆቻችንን ያጣንበት ዓመት ታይቶ አይታወቅም።” የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

ባሕር ዳር፡ መስከረም 4/2012 ዓ.ም (አብመድ) በተያዘው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ መማር ማስተማርን እውን ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ባለፈው የትምህርት ዘመን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ማለፋቸውን ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች በሐሳብ ልዕልና በመከራከር መተማመን ሲችሉ ከውጭ የሚነሱ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ምክንያት በማድረግ ሲከሰቱ የነበሩ ትምህርታቸውን ማስተጓጎል፣ በቡድን መደባደብና መገዳደል አሳዛኝ ክስተቶች እንደነበሩ ፕሮፌሰር አፈወርቅ አስታውሰዋል፡፡

“በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ታሪክ እንደ 2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ብዙ ልጆቻችንን ያጣንበት ዓመት ታይቶ አይታወቅም” ያሉት ፕሮፌሰር አፈወርቅ፣ ከዚህ በመማርም ከሁሉም የክልል አመራሮችና ከዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢዎች ጋር በ2012 የትምህርት ዘመን ሊወሰዱ በሚገባቸው ጥንቃቄዎች ላይ ውይይት መደረጉን ገልፀዋል።

በዚህም እያንዳንዱ ወላጅ፣ ተማሪ እና በየደረጃው ያለ አስተዳደር ለሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Previous articleሰላማዊ ሰልፎቹ በሰላም ተጠናቅቀዋል፡፡
Next articleበኩር ነሐሴ 06 ቀን 2011ዓ.ም ዕትም