
338 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) 338 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ወደ ሀገራቸው ዛሬ
ተመልሰዋል።
በተለያዩ ሀገራት በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት
ጋር በመተባበር እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡
ለተመላሾቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው
አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m