የኢትዮ-ጃፓን የንግድ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሠሩ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ገለጹ፡፡

251

የኢትዮ-ጃፓን የንግድ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሠሩ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ገለጹ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 09/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢፌዴሪ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የጃፓን
አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር የሀገራቱን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ተወያይተዋል፡፡
አቶ መላኩ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እና መልካም ዕድሎችን ለአምባሳደሯ አብራርተዋል፡፡ ጃፓን እና
ኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ ዲፕሎማሲ እና የንግድ ግንኙነት እንዳላቸውም በውይይታቸው አንስተዋል፡፡
ተወዳዳሪነትን የሚጨምሩ የቴክኖሎጂ መሻሻያዎች መደረጋቸውንም ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡
አምባሳደር ኢቶ በበኩላቸው የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እና በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ፣ በአቅም ግንባታ
እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ድጋፍ ለመስጠት ጃፓን ያላትን ፍላጎት አረጋግጠዋል፡፡
ምንጭ፡- የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
በየማብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleግብጽና ሱዳን የህዳሴ ግድብን ለውስጥ የፖለቲካ ችግሮቻቸው መፍትሔ ለማድረግ እየጣሩ እንደሚገኙ ምሁራን ገለጹ፡፡
Next articleአዲሱን የአጠቃላይ ሥርዓተ-ትምህርት ወደ ተግባር ለማስገባት የሚያስችል ሰነድ ተዘጋጀ፡፡