አሜሪካ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ሶስቱም ሀገራት ካልጋበዟት በስተቀር ጣልቃ እንደማትገባ አስታወቀች፡፡

354

አሜሪካ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ሶስቱም ሀገራት ካልጋበዟት በስተቀር ጣልቃ እንደማትገባ
አስታወቀች፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 09/2013 ዓ.ም (አብመድ) አሜሪካ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ሶስቱም
ሀገራት ካልጋበዟት በስተቀር አገራቱን ለማደራደር ጣልቃ እንደማትገባ አስታውቃለች፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት
የቀጣናዊ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ሳሙኤል ዋርበርግ “ቴን” በተባለ የግብጽ የሳተላይት ቴሌቪዥን ላይ በሚሰራጨው “ፔን ኤንድ
ፔፐር” ዝግጅት በበይነ መረብ በሰጡት ማብራሪያ፤ የአባይ ወንዝ ለግብጽ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ለሱዳንም በጣም ጠቃሚ
ወንዝ መሆኑን አሜሪካ ታምናለች ብለዋል።
በሀገራቱ መካከል ያለው ልዩነት በውይይትና በድርድር እንዲፈታ ሀገራቸው ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል ቃል አቀባዩ
ገልጸዋል። ቃል አቀባዩ አያይዘውም፤ አሜሪከ ሶስቱም ሀገራት ጥሪ ካደረጉላት የሚጠበቅባትን አዎንታዊ ሚና ለመወጣት ዝግጅት
እያደረገች መሆኗን ነው የገለጹት።
አሜሪካ በግድቡ ዙሪያ ያሉ አለመግባባቶች መፈታት ያለባቸው በሶስቱ ሀገራት ብቻ ነው የሚል አቋም እንዳላት የገለጹት ቃል
አቀባዩ፤ ሀገራቸው በሶስቱ ሀገራት ጥሪ ካልቀረበላት በስተቀር ጣልቃ እንደማትገባ ማስታወቃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

Previous articleባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በትብብር ለመሥራት ተስማሙ።
Next articleግብጽና ሱዳን የህዳሴ ግድብን ለውስጥ የፖለቲካ ችግሮቻቸው መፍትሔ ለማድረግ እየጣሩ እንደሚገኙ ምሁራን ገለጹ፡፡