ባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በትብብር ለመሥራት ተስማሙ።

386

ባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በትብብር ለመሥራት ተስማሙ።
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 09/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ኢትዮጵያዊያን በእኩልነት፣ በፍሕና በሠላም
የሚተዳደሩበትን ዘላቂ ሥርዓት ለማስፈን እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ስትራቴጂክ ግቡም ኢትዮጵያዊያንን ፍትሐዊ
ተጠቃሚ ማድረግ፣ ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ የፖለቲካ ማዕቀፍ እንዲፈጠር ነዉ ብሏል።
ባልደራስ ለእዉነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ደግሞ የኢትዮጵያዊ ኅብር አይነተኛ መገለጫ የሆነችው የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ራሱን
በራሱ የማስተዳደር መብቱ እንዲረጋገጥ ማስቻል እንደሆነ ገልጿል።
በመጪው ሀገራዊ ምርጫ የመራጮችን የጋራ ፍላጎትና ራዕይ ለማሳካት በጋራ ለመሥራት በማሰብ የተመሰረተ የፖለቲካ ትብብር
መሆኑን በጋራ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ለትብብሩ ሕጋዊ እዉቅና እንዲሠጠዉም በመግለጫቸው ጠይቀዋል።
በሀገሪቱ የሚፈጸሙ የሽብር ድርጊቶች እንዲቆሙ፣ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ መፈናቀል እና የንብረት መዉደምን መንግሥት
መቆጣጠር እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
በተለይ ችግሩ ተባብሶ የሚገኝባቸዉ ኦሮሚያ፣ የቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ እና አንዳንድ የደቡብ ክልል አካባቢዎች የሚገኙ የመንግሥት
አስተዳደር፣ የጸጥታ አካላት ኀላፊነት ይዉሰዱ ብለዋል።
በትግራይ ክልል ሰብዓዊ መብት እንዲከበር እና የሰብዓዊ እርዳታ በተገቢዉ መልኩ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል። ለእስር የተዳረጉ
የባልደራስ አመራሮች እንዲፈቱም በጋራ በሰጡት መግለጫ ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ጽዮን አበበ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየጨጨሆ ከተማን የንጹህ መጠጥ ውኃ ችግር በሁለት ወራት ውሥጥ እንደሚፈታ የነፋስ መውጫ ከተማ አሥተዳደር ውኃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት አሥታወቀ፡፡
Next articleአሜሪካ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ሶስቱም ሀገራት ካልጋበዟት በስተቀር ጣልቃ እንደማትገባ አስታወቀች፡፡