
“እንደ ሀገር ብዙ ሀብት ወጥቶባቸዉ የሚደረጉ የምርምር ሥራዎች የፈጠራና ግኝቶች መነሻና ለትምህርት ሥራም አጋዥ መሆን ይገባቸዋል” የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 08/2013 ዓ.ም (አብመድ) በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና እቅዶች ላይ ለሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኅበረሰብ የግንዛቤ ማስጨባጫ ተጀምሯል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጠዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ በትምህርት ጥራት፤ በተቋማት ትስስርና ምርምር ሥራዎች ላይ መምህራን ለዘርፉ እድገት አሻራቸዉን የሚያኖሩበት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡
“እንደ ሀገር ብዙ ሀብት ወጥቶባቸዉ የሚደረጉ የምርምር ሥራዎች የፈጠራና ግኝቶች መነሻና ለትምህርት ሥራም አጋዥ መሆን ይገባዋቸዋል” ነው ያሉት፡፡
መሪ መሪነቱ የሚረጋገጠዉ ተቋማዊ አቅም ገንብቶ ቀጣይነት ያለዉ ተቋም መፍጠር ሲችል ነዉ ያሉት ሚኒስትሩ በፖሊሲና ስትራቴጂዎችም ሆነ በአመራር ዘርፍ የዩኒቨርስቲ ማኅበረሰቡን አቅም የመገንባት ሥራ በዩኒቨርስቲ መሪዎች ተጀምሮ በየደረጃዉ ያሉ የሥራ ኀላፊዎችን አካቶ እያደገ የሚሄድ በመሆኑ ለተፈጻሚነቱም በትኩረት እንዲሠሩ አሳስበዋል፡፡
“የጠራ የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ እቅድ፣ ፕሮግራሞች እና ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ግንዛቤ እና ትግበራ ለኢትዮጵያ ዕድገት፣ ልማትና ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀዉ ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ በሳይንስ፣ በከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂ ብሎም በ10 አመት መሪ የልማት እቅድ ላይ እንደሚያተኮር ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
