የታላቁ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 79 በመቶ ደረሰ፡፡

517

የታላቁ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 79 በመቶ ደረሰ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 08/2013 ዓ.ም (አብመድ) የህዳሴ ግድብ 10ኛ ዓመትን በማስመልከት በውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ
አስተባባሪነት በግድቡ ድርድር ላይ የተሳተፉ፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ምሁራን እንዲሁም ከፍተኛ የሥራ
ኀላፊዎች የተገኙበት ሲምፖዝየም እየተካሄደ ነው፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንተናገሩት የህዳሴ ግድብ የመላው ኢትዮጵያውያን
አንጡራ ሃብት ነው። ይህንን ሃብት ወደ ልማት ለመቀየርና ለመጠቀም ባለፉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ብዙ ውጣ ውረድ
ማለፋቸውን አስታውሰዋል።
“በዓባይ ወንዝ 86 በመቶ ድርሻ ያላትን ኢትዮጵያ የፍትሐዊ ተጠቃሚነት መብቷን ማንም ሊነጥቃት አይችልም” ሲሉም
ተናግረዋል።
የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ስለሺ በቀለ ኢትዮጵያ እስከአሁን ዓለም ዓቀፍ የወሰን ተሻጋሪ ውኃ አጠቃቀም ሕጎችን
በማክበር መርህ ስትንቀሳቀስ መቆየቷን ገልጸዋል። ነገር ግን ከተደራዳሪ ሀገሮች ጋር በትብብር ለመሥራት የምታደርገው ጥረት
በጎ ምላሽ እያስገኘ እንዳልሆነ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የፍትሐዊ ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ እንደምትሠራ ተናግረዋል።
የወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ያላቸው ሀገሮችም ተመሳሳይ የሆነ የፍትሐዊ ተጠቃሚነት መርህ መከተል እንደሚገባቸውም
አስገንዝበዋል።
እየተካሄደ ባለው ሲምፖዚየም የሦስትዮሽ የድርድር ሂደትን የሚዳስሱ የውይይት መነሻ ሃሳቦች በተደራዳሪዎች ቀርቦ ውይይት
ይደረጋል ተብሏል።
በመድረኩ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ ተደራዳሪዎች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣
የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እንደተገኙ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“የህዳሴ ግድብ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ነው” የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ
Next articleበምርጫ ወቅት ብዙኃን መገናኛ ተቋማት በኀላፊነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ምሁራን ገለፁ፡፡