
“የህዳሴ ግድብ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ነው” የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ጽሕፈት ቤት
ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 08/2013 ዓ.ም (አብመድ) መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራቸው የልማት ሥራዎች መካከል
በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰውን የህዳሴ ግድብ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን የህዳሴ ግድብ
ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ገለጹ።
ዶክተር አረጋዊ እንደተናገሩት የህዳሴው ግድብ የሀገሪቱ ተስፋ መሆኑን ከህፃን እስከ አዋቂ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል
ስላመነበት አሁን ላይ ሥራው እንዲጠናቀቅ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል።
ሕዝቡ በጉልበቱ፣ በእውቀቱ እና ባለው ሁሉ የግድቡን ሥራ እያገዘ እንደሆነ ያመለከቱት ዶክተር አረጋዊ በመንግሥት በኩል
የሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችንም በትኩረት እየተከታተለ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ በነበሩባት የውስጥ የቤት ሥራዎቿ ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ በውኃዋ ሳትጠቀም ቆይታለች ያሉት ዶክተር አረጋዊ፣
አሁን ደግሞ ጊዜው ደርሶ አልምታ ለመጠቀም እየሠራች ነው። በዚህ ሀብቷ አትጠቀሚ ማለት ከፍተኛ ስህተት ከመሆኑም በላይ
የቀኝ ግዛት ሥነ ልቦና የፈጠረው ችግር መሆኑን አመልክተዋል።
“ሱዳንና ግብጽ አሁን እያነሱ ያለው አጀንዳ መሰረታዊ አይደለም ምክንያቱም ለብዙ ዘመናት ውኃውን ብቻ ሳይሆን አፈራችንንም
በአግባቡ ተጠቅመውበታል፤ አሁን ደግሞ ጊዜው በጋራ የመልማት ነው” ብለዋል ዶክተር አረጋዊ፡፡ ዘገባው የኢትዮጵያ ፕረስ
ድርጅት ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
