
“የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በከፈለው መስዋዕትነት ኢትዮጵያን ከብተና ያዳነ ኃይል ነው” የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር
አገኘሁ ተሻገር
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 07/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እንዳሉት ሠራዊቱ በሕግ
ማስከበርና የህልውና ዘመቻው የፈፀመው ግዳጅ ህዝቡ ለሠራዊቱ የነበረውን የተዛባ አተያይ ያከመበት ነው። “ከሃዲው የጁንታ
ቡ1ድን ስብስቦች በሀገሪቱ በየደረጃው የሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች ጣምራ ክንድ ፈጥረው ለጋራ ሰላማችን እንዳይተጉ መዋቅራዊ
አደረጃጀት በመዘርጋት የአፍራሽነት ሚና ሲወጡ ነበር” ብለዋል።
የህወሓት ኃይሎች በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ይከሰቱ የነበሩ ዘርና ብሔር ተኮር ግጭቶችን ከመወጠን ጀምሮ የእኩይ
ዓላማቸው ፈፃሚ የሆኑ ኃይሎችን በመመልመል ፣ በማሰልጠንና በማሰማራት የሕዝቦችን አብሮነታዊ ሰላምና ማንነታዊ አንድነት
ሲያደፈርሱ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
በሕግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻው መላው የአማራ ሕዝብ ፣ ባለሃብቶች ፣ የህክምና ባለሙያዎች እና በየከተሞቹ የሚገኙ
እናቶች የላቀ አስተዋፅኦ አበርክተዋል ነው ያሉት አቶ አገኘሁ።
“የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በከፈለው መስዋዕትነት ኢትዮጵያን ከብተና ያዳነ ኃይል ነው” ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።
“ልክ እንደ ከሃዲ ጁንታዎች ሁሉ አሁን ላይ የሌላ ኃይል ጉዳይ አስፈፃሚ የሆኑትን የሱዳን ተንኳሽ ኃይሎችን ጨምሮ እየታዩ ካሉ
ሀገራዊና ከባቢያዊ አዝማሚያዎች አንፃር እንደ ሀገር ሕብረታችንን አጠናክረን ከሠራዊታችን ጎን የምንቆምበትን ነው” ብለዋል፡፡
የአማራ ሕዝብና መንግሥት በየትኛውም መልኩ በሚያስፈልጉ ድጋፎች ሁሉ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጎን እንደሚቆሙ ርእሰ
መሥተዳድሩ መግለጻቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
